ሐዋርያት ሥራ 17:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምነው የተከተሉት ሰዎችም ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ ከአርዮስፋጎስ ባለሥልጣኖች ወገን የሚሆን ዲዮናስዮስ ነበር፤ ደማሪስ የምትባል ሴትም ነበረች፤ ሌሎችም አብረዋቸው ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዳንድ ሰዎች ግን ጳውሎስ ባለው በመስማማት ተከተሉት፤ አመኑም፤ ከእነዚህም ዲዮናስዮስ የተባለው የአርዮስፋጎስ ፍርድ ቤት አባል፣ ደማሪስ የተባለች ሴትና ሌሎችም ሰዎች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንዳንዶች ወንዶች ግን ተባብረው አመኑ፤ ከእነርሱ ደግሞ በአርዮስፋጎስ ያለው የፍርድ ቤት ፈራጅ ዲዮናስዮስ ደማሪስ የሚሉአትም አንዲት ሴት ሌሎችም ከእነርሱ ጋር ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዳንድ ሰዎች ግን ከእርሱ ጋር ተባበሩና አመኑ፤ ካመኑትም ሰዎች መካከል የአርዮስፋጎስ ጉባኤ አባል የሆኑት ዲዮናስዮስ የተባለ ሰውና ደማሪስ የተባለች አንዲት ሴት፥ ሌሎችም ይገኙባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዳንዶች ወንዶች ግን ተባብረው አመኑ፤ ከእነርሱ ደግሞ በአርዮስፋጎስ ያለው የፍርድ ቤት ፈራጅ ዲዮናስዮስ ደማሪስ የሚሉአትም አንዲት ሴት ሌሎችም ከእነርሱ ጋር ነበሩ። |
አሕዛብም ይህን ሰምተው ደስ አላቸው፤ የእግዚአብሔርንም ቃል አከበሩ፤ ለዘለዓለም ሕይወትም የተዘጋጁ ሁሉ አመኑ።
ይዘውም አርዮስፋጎስ ወደሚባል ሸንጎ ወሰዱት፤ እንዲህም አሉት፥ “ይህን የምታስተምረውን አዲስ ትምህርት እናውቅ ዘንድ ይቻለናልን? እስቲ ንገረን?
ጳውሎስም በአርዮስፋጎስ ውስጥ ቆሞ እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ የአቴና ሰዎች! በሥራችሁ ሁሉ አማልክትን ማምለክ እንደምታበዙ አያችኋለሁ።
ከእነርሱና ከደጋጎች አረማውያንም ብዙ ሰዎች፥ ከታላላቆች ሴቶችም ጥቂቶች ያይደሉ አምነው ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ሆኑ።