ከይሁዳ ሀገርም የወረዱ ሰዎች፥ “እንደ ሙሴ ሕግ ካልተገዘራችሁ ልትድኑ አትችሉም” እያሉ ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 15:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም አንብበው እጅግ ደስ አላቸው፥ ተጽናኑም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡም ካነበቡት በኋላ አበረታታች በሆነው ቃሉ ደስ ተሠኙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባነበቡትም ጊዜ ከምክሩ የተነሣ ደስ አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አማኞቹም ደብዳቤውን ባነበቡ ጊዜ በሚያጽናናው መልእክት እጅግ ደስ አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባነበቡትም ጊዜ ከምክሩ የተነሣ ደስ አላቸው። |
ከይሁዳ ሀገርም የወረዱ ሰዎች፥ “እንደ ሙሴ ሕግ ካልተገዘራችሁ ልትድኑ አትችሉም” እያሉ ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር።
አሁንም እግዚአብሔርን አትፈታተኑት፤ እኛም አባቶቻችንም ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ ለምን ትጭናላችሁ?
ግዙራንስ እግዚአብሔርን በመንፈስ የምናገለግለውና የምናመልከው እኛ ነን፤ እኛም በኢየሱስ ክርስቶስ እንመካለን እንጂ በሥጋችን የምንመካ አይደለም።