ሐዋርያት ሥራ 14:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ፥ “አማልክት ሰዎችን መስለው ወደ እኛ ወረዱ” እያሉ በሊቃኦንያ ቋንቋ ጮኹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ፣ በሊቃኦንያ ቋንቋ፣ “አማልክት በሰው ተመስለው ወደ እኛ ወርደዋል!” ብለው ጮኹ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በሊቃኦንያ ቋንቋ “አማልክት ሰዎችን መስለው ወደ እኛ ወርደዋል፤” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎቹም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ፥ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “አማልክት በሰው አምሳል ሆነው ወደ እኛ ወርደዋል!” በማለት በሊቃኦንያ ቋንቋ ተናገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በሊቃኦንያ ቋንቋ፦ “አማልክት ሰዎችን መስለው ወደ እኛ ወርደዋል” አሉ፤ |
እነርሱ ግን ወዲያውኑ የሚያብጥ ወይም ሞቶ የሚወድቅ መስሎአቸው ነበር። እያዩትም ብዙ ሰዓት ቆሙ፤ አንዳችም እንደ አልጐዳው በአዩ ጊዜም፥ “ይህስ አምላክ ነው” ብለው ቃላቸውን ለወጡ።