በዚያን ጊዜ አንካሳዎች እንደ ሚዳቋ ይዘልላሉ፤ የዲዳዎችም ምላስ ርቱዕ ይሆናል፤ በምድረ በዳ ውኃ፥ በተጠማ መሬትም ፈሳሽ ይፈልቃልና።
ሐዋርያት ሥራ 14:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድምፁንም ከፍ አድርጎ፥ “ተነሥና ቀጥ ብለህ በእግርህ ቁም እልሃለሁ” አለው፤ ወዲያውኑም ተነሥቶ ተመላለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በታላቅ ድምፅ፣ “ቀጥ ብለህ በእግርህ ቁም!” አለው፤ በዚህ ጊዜ ዘልሎ ተነሣና መራመድ ጀመረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በታላቅ ድምፅ “ቀጥ ብለህ በእግርህ ቁም፤” አለው። ብድግ ብሎም ተንሥቶ ይመላለስ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ቀጥ ብለህ በእግርህ ቁም!” ሲል በታላቅ ድምፅ ተናገረ፤ ሰውየውም ብድግ አለና መራመድ ጀመረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በታላቅ ድምፅ፦ “ቀጥ ብለህ በእግርህ ቁም” አለው። ብድግ ብሎም ተንሥቶ ይመላለስ ነበር። |
በዚያን ጊዜ አንካሳዎች እንደ ሚዳቋ ይዘልላሉ፤ የዲዳዎችም ምላስ ርቱዕ ይሆናል፤ በምድረ በዳ ውኃ፥ በተጠማ መሬትም ፈሳሽ ይፈልቃልና።
“እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ በእኔ የሚያምን እኔ የምሠራውን ሥራ እርሱም ይሠራል፤ ከዚያም የሚበልጥ ይሠራል፤ እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና።
እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውኃ በውስጡ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆንለታል እንጂ።”