ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ፥ ልጆቹንና ቤቱን ያዝዛቸው ዘንድ እንዳለው አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር ለአብርሃም የተናገረውን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ ነው።”
ሐዋርያት ሥራ 13:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አለው፥ “ሽንገላንና ክፋትን ሁሉ የተመላህ፥ የሰይጣን ልጅ፥ የጽድቅ ሁሉ ጠላት ሆይ፥ የቀናውን የእግዚአብሔርን መንገድ ማጣመምህን ትተው ዘንድ እንቢ አልህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንተ የጽድቅ ሁሉ ጠላት፣ ተንኰልንና ክፋትን ሁሉ የተሞላህ የዲያብሎስ ልጅ፣ የጌታን ቀና መንገድ ከማጣመም አታርፍምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አንተ ተንኰል ሁሉ ክፋትም ሁሉ የሞላብህ፥ የዲያብሎስ ልጅ፥ የጽድቅም ሁሉ ጠላት፥ የቀናውን የጌታን መንገድ ከማጣመም አታርፍምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንተ የዲያብሎስ ልጅ! የእውነት ሁሉ ጠላት! ማታለልና ክፋት ሁሉ የሞላብህ፥ ቀጥተኛውን የጌታን መንገድ ማጣመም አትተውምን! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “አንተ ተንኰል ሁሉ ክፋትም ሁሉ የሞላብህ፥ የዲያብሎስ ልጅ፥ የጽድቅም ሁሉ ጠላት፥ የቀናውን የጌታን መንገድ ከማጣመም አታርፍምን? |
ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ፥ ልጆቹንና ቤቱን ያዝዛቸው ዘንድ እንዳለው አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር ለአብርሃም የተናገረውን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ ነው።”
በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”
ልቡም በእግዚአብሔር መንገድ ከፍ ከፍ አለ፤ የኮረብታውን መስገጃዎችና የማምለኪያ አፀዱንም ከይሁዳ አስወገደ።
ከፀሓይ በታች የተደረገው ክፉ ሁሉ ለሁሉ ነው፤ የሁሉ ድርሻ አንድ ነውና። ደግሞም የሰው ልጆች ልብ ክፋትን ትሞላለች፥ በሕይወታቸው ሳሉ ሁከት በልባቸው አለ፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሙታን ይወርዳሉ።
ለሰው ሁሉ ቃሉ ሸክም ይሆንበታልና የእግዚአብሔር ሸክም ብላችሁ ከእንግዲህ ወዲህ አትጥሩ፤ የሠራዊትን ጌታ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን የሕያውን አምላክ ቃል ለውጣችኋልና።
ከእንግዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤፍሬም ምንድን ነው? እኔ አደከምሁት፤ አጸናሁትም፤ እኔ እንደ ተወደደ አበባ አፈራዋለሁ፤ ፍሬህም በእኔ ዘንድ ይገኛል።
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።
ዳሩ ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ወደ ጥምቀቱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፥ እንዲህ አላቸው “እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው ቍጣ እንድትሸሹ ማን አመለከታችሁ?
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “እናንተ ፈሪሳውያን፥ ዛሬ የጽዋውንና የወጭቱን ውጭውን ታጥቡታላችሁ፤ ታጠሩታላችሁም፤ ውስጡ ግን ቅሚያንና ክፋትን የተመላ ነው።
እናንተ ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ወዮላችሁ! የጽድቅንና የዕውቀትን መክፈቻ ወስዳችሁ ትሰውራላችሁና፤ እናንተም አትገቡምና፤ የሚገቡትንም መግባትን ትከለክሉአቸዋላችሁ።”
እርሱም፥ “ነቢዩ ኢሳይያስ እንደ ተናገረ የእግዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ እያለ በምድረ በዳ የሚሰብክ የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እኔ ነኝ” አለ።
እናንተስ ከአባታችሁ ከሰይጣን ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፈቃድ ልታደርጉ ትወዳላችሁ፤ እርሱ ከጥንት ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በእውነትም አይቆምም፤ በእርሱ ዘንድ እውነት የለምና፤ ሐሰትንም በሚናገርበት ጊዜ ከራሱ አንቅቶ ይናገራል፤ ሐሰተኛ ነውና፤ የሐሰትም አባት ነውና።
ነገር ግን እባብ ሔዋንን በተንኰሉ እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ከክርስቶስ የዋህነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ።
እንግዲህ በሽንገላቸው ያስቱ ዘንድ በሚተናኰሉ ሰዎች ተንኰል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ ወዲያና ወዲህ እየተፍገመገምንና እየተንሳፈፍን ሕፃናት አንሁን።