ሐዋርያት ሥራ 12:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ አስገደለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሐንስን ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ አስገደለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው። |
ኤልያስም፥ “ሁሉን ለሚገዛ ለእግዚአብሔር እጅግ ቀንቻለሁ፤ የእስራኤል ልጆች ቃል ኪዳንህን ትተዋልና፥ መሠዊያዎችህንም አፍርሰዋልና፥ ነቢያትህንም በሰይፍ ገድለዋልና፤ እኔም ብቻዬን ቀርቻለሁ ነፍሴንም ሊወስዱአት ይሻሉ” አለ።
ከግብፅም ኡርያን አውጥተው ወደ ንጉሡ ወደ ኢዮአቄም ይዘውት መጡ፤ እርሱም በሰይፍ ገደለው፤ ሬሳውንም በሕዝብ መቃብር ጣለው።
በመጋዝ የሰነጠቁአቸው፥ በድንጋይ የወገሩአቸው፥ በሰይፍም ስለት የገደሉዋቸው አሉ፤ ማቅ፥ ምንጣፍና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ተጨነቁ፤ ተቸገሩ፤ መከራ ተቀበሉ፤ ተራቡ፥ ተጠሙም።