እርሱ ግን ዝም እንዲሉ በእጁ አመለከታቸው፤ ከወኅኒ ቤትም እግዚአብሔር እንደ አወጣው ነገራቸው፤ “ይህንም ለያዕቆብና ለወንድሞች ሁሉ ንገሩ” አላቸው፤ ከዚያም ወጥቶ ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።
ሐዋርያት ሥራ 12:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋ ጊዜም ወታደሮች፥ “ጴጥሮስ ምን ሆነ?” ብለው ታወኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ጧት ወታደሮቹ፣ “ጴጥሮስ የት ገባ?” እያሉ በመካከላቸው ትልቅ ትርምስ ተፈጠረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነጋም ጊዜ “ጴጥሮስን ምን አግኝቶት ይሆን?” ብለው በጭፍሮች ዘንድ ብዙ ሁከት ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በነጋም ጊዜ ወታደሮቹ “ጴጥሮስ ምን ደርሶበት ይሆን?” በማለት እጅግ ታወኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጋም ጊዜ፦ “ጴጥሮስን ምን አግኝቶት ይሆን?” ብለው በጭፍሮች ዘንድ ብዙ ሁከት ሆነ። |
እርሱ ግን ዝም እንዲሉ በእጁ አመለከታቸው፤ ከወኅኒ ቤትም እግዚአብሔር እንደ አወጣው ነገራቸው፤ “ይህንም ለያዕቆብና ለወንድሞች ሁሉ ንገሩ” አላቸው፤ ከዚያም ወጥቶ ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።
ሄሮድስ ግን አስፈልጎ ባጣው ጊዜ ጠባቂዎችን መረመረ፤ ይገድሉአቸውም ዘንድ አዘዘ፤ ከዚህም በኋላ ከይሁዳ ወደ ቂሳርያ ወርዶ በዚያ ተቀመጠ።
የወህኒ ቤቱ ጠባቂም ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ በሮች ሁሉ ተከፍተው አየ፤ ሰይፉንም መዝዞ ራሱን ሊገድል ወደደ፤ እስረኞቹ ያመለጡት መስሎት ነበርና።