ሐዋርያት ሥራ 11:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ በርናባስ ሳውልን ሊፈልግ ወደ ጠርሴስ ሄደ፤ በአገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ ወሰደው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ በርናባስ፣ ሳውልን ለመፈለግ ወደ ጠርሴስ ሄደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በርናባስም ሳውልን ሊፈልግ ወደ ጠርሴስ ወጣ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ በርናባስ ሳውልን ለመፈለግ ወደ ጠርሴስ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በርናባስም ሳውልን ሊፈልግ ወደ ጠርሴስ መጣ፤ |
ጳውሎስም፥ “እኔስ አይሁዳዊ ሰው ነኝ፤ የተወለድሁባትም ሀገር ጠርሴስ የታወቀች የቂልቅያ ከተማ ናት፤ ለሕዝቡም እንድነግራቸው ትፈቅድልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ” አለው።
በሐዋርያትም ዘንድ ትርጓሜዉ የመጽናናት ልጅ የሚሆን በርናባስ የተባለ የሌዊ ወገን ስሙን ዮሴፍ የሚሉት አንድ የቆጵሮስ ሰው ነበር።
ጌታም፥ “ተነሣና ቅን በምትባለው መንገድ ሂድ፤ በይሁዳ ቤትም ከጠርሴስ ሀገር የመጣ ሳውል የሚባል ሰው ፈልግ፤ እርሱ አሁን ይጸልያልና” አለው።
በርናባስም አግኝቶ ወደ ሐዋርያት ወሰደው፤ ጌታችንም በመንገድ እንደ ተገለጠለትና እንደ አነጋገረው፥ በደማስቆም በኢየሱስ ስም እንደ አስተማረ ነገራቸው።