ሐዋርያት ሥራ 10:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ጴጥሮስ የሚባለውን ስምዖንን ይጠሩልህ ዘንድ ወደ ኢዮጴ ከተማ ሰዎችን ላክ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም ሰዎችን ወደ ኢዮጴ ልከህ ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንን አስመጣው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ልከህ ጴጥሮስ የሚባለውን ስምዖንን አስመጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁንም ሰዎችን ወደ ኢዮጴ ላክና ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንን አስጠራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ልከህ ጴጥሮስ የሚባለውን ስምዖንን አስመጣ። |
አሁንም ወደ ኢዮጴ ከተማ ላክና በባሕር አቅራቢያ ባለችው በቍርበት ፋቂው በስምዖን ቤት የሚኖረውን ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንን ይጥሩልህ፤ እርሱ መጥቶ የምትድንበትን ይነግርሃል።
ብዙ ክርክርም ከተከራከሩ በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው፥ “ወንድሞች ሆይ፥ ስሙ፤ ለአሕዛብ ከአፌ የወንጌሉን ቃል እንዳሰማቸውና እንዲያምኑ እግዚአብሔር አስቀድሞ እንደ መረጠኝ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።
ለጳውሎስም በሌሊት አንድ መቄዶናዊ ሰው ቁሞ፥ “ወደ እኛ ወደ መቄዶንያ ዕለፍና ርዳን” እያለ ሲማልደው በራእይ ተገለጸለት።
በኢዮጴ ሀገርም ጣቢታ የምትባል አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፤ በትርጓሜውም ዶርቃስ ይሉአታል፤ ፌቆ ማለት ነው፤ እርስዋም ብዙ ደጋግ ሥራ ትሠራ ነበር፤ ምጽዋትም ትሰጥ ነበር።
ልዳም ለኢዮጴ ቅርብ ነበርና ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ በዚያ እንዳለ ሰምተው ወደ እነርሱ መምጣት እንዳይዘገይ ይማልዱት ዘንድ ሁለት ሰዎችን ወደ እርሱ ላኩ።