ሁሉም እያንዳንዱ የወደረኛውን ራስ በእጁ ያዘ፤ ሰይፉንም በወደረኛው ጐን ሻጠ፤ ተያይዘውም ወደቁ። የዚያም ስፍራ ስም “በገባዖን የሸመቁ ሰዎች ድርሻ” ተብሎ ተጠራ፤
ሐዋርያት ሥራ 1:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ዜናዉ ተሰማ፤ ያም መሬት በቋንቋቸው አኬልዳማ ተብሎ ተጠራ፤ ይኸውም የደም መሬት ማለት ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም በኢየሩሳሌም በሚኖሩት ሁሉ ዘንድ ተሰማ፤ መሬቱም በቋንቋቸው “አኬልዳማ” ተብሎ ተጠራ፤ ትርጓሜውም “የደም መሬት” ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ሁሉ ታወቀ፤ ስለዚህም ያ መሬት በቋንቋቸው አኬልዳማ ተብሎ ተጠራ፤ እርሱም የደም መሬት ማለት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ነገር በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ ታወቀ፤ ስለዚህ ያ መሬት በቋንቋቸው ‘አኬልዳማ’ ተብሎ ተጠራ፤ ትርጓሜውም ‘የደም መሬት’ ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ሁሉ ታወቀ፤ ስለዚህም ያ መሬት በቋንቋቸው አኬልዳማ ተብሎ ተጠራ፥ እርሱም የደም መሬት ማለት ነው። |
ሁሉም እያንዳንዱ የወደረኛውን ራስ በእጁ ያዘ፤ ሰይፉንም በወደረኛው ጐን ሻጠ፤ ተያይዘውም ወደቁ። የዚያም ስፍራ ስም “በገባዖን የሸመቁ ሰዎች ድርሻ” ተብሎ ተጠራ፤
እግዚአብሔርም፦ የተስማሙበትን የከበረውን ዋጋዬን በግምጃ ቤቱ ውስጥ አኑረው አለኝ። እኔም ሠላሳውን ብር ወስጄ በእግዚአብሔር ቤት ባለው በግምጃ ቤቱ ውስጥ አኖርሁት።
“እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ነገር ስሙ፤ እንደምታውቁት በመካከላችሁ እግዚአብሔር በእጁ ባደረገው በከሃሊነቱ በተአምራቱና በድንቅ ሥራዎቹ እግዚአብሔር የገለጠላችሁን ሰው የናዝሬቱን ኢየሱስን ስሙ።
በፈቀደለትም ጊዜ ጳውሎስ በደረጃው ላይ ቆሞ እጁን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ፤ እጅግም ጸጥታ በሆነ ጊዜ ጳውሎስ በዕብራይስጥ ቋንቋ ተናገረ፤ እንዲህም አለ።