3 ዮሐንስ 1:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሽማግሌው በእውነት እኔ ለምወደው ለተወደደው ለጋይዮስ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሽማግሌው፤ በእውነት ለምወድደው ለውድ ወዳጄ ለጋይዮስ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሽማግሌው፥ በእውነት ለምወደው ለተወደደው ለጋይዮስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእውነት ለማፈቅረው፥ ለተወደደው ጋይዮስ፥ ከእኔ ከሽማግሌው የተላከ መልእክት፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሽማግሌው በእውነት እኔ ለምወደው ለተወደደው ለጋይዮስ። |
ከተማውም ሁሉ ታወከ፤ የመቄዶንያን ሰዎች የጳውሎስን ወዳጆች ጋይዮስንና አርስጥሮኮስንም ከእነርሱ ጋር እየጐተቱበአንድነት ወደ ጨዋታው ቦታ ሮጡ።
ከእርሱም ጋር የቤርያ ሀገር ሰው የሚሆን ሱሲጳጥሮስ፥ የተሰሎንቄም ሰዎች አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ፥ የደርቤኑ ሰው ጋይዮስና ጢሞቴዎስም፥ የእስያ ሰዎች የሚሆኑ ቲኪቆስና ጥሮፊሞስም አብረውት ሄዱ።
እኔንና አብያተ ክርስቲያናትን ሁሉ በእንግድነት የተቀበለ ጋይዮስም ሰላም ብሎአችኋል፤ የከተማው መጋቢ አርስጦስና ወንድማችን ቁአስጥሮስም ሰላም ብለዋችኋል።
እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤