La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ጢሞቴዎስ 2:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በውትድርና የሚያገለግል ሰው አዛዡን ለማስደሰት ይጥራል እንጂ በሌላ ሥራ ራሱን አያጠላልፍም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በማገልገል ላይ ያለ ማንም ወታደር፥ ዐላማው ለወታደርነት የመለመለውን ሰው ለማስደሰት እስከሆነ ድረስ፥ እንደ ማናቸውም ሰው በዕለት ተዕለት ጉዳዮች አይጠመድም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በወታደርነት የሚያገለግል ሰው የጦር አዛዡን ለማስደሰት ዝግጁ መሆን አለበት እንጂ ወታደራዊ ባልሆነ ጉዳይ ላይ አይውልም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም።

Ver Capítulo



2 ጢሞቴዎስ 2:4
11 Referencias Cruzadas  

በእ​ሾ​ህም መካ​ከል የወ​ደ​ቀው ቃሉን ሰም​ተው የባ​ለ​ጠ​ግ​ነት ዐሳብ፥ የኑ​ሮም መቈ​ር​ቈር የተ​ድ​ላና የደ​ስታ መጣ​ፈ​ጥም የሚ​አ​ስ​ጨ​ን​ቃ​ቸ​ውና ፍሬ የማ​ያ​ፈሩ ናቸው።


አሁ​ንም ብን​ኖ​ርም፥ ብን​ሞ​ትም እር​ሱን ደስ ለማ​ሰ​ኘት እን​ጥ​ራ​ለን።


እን​ግ​ዲህ ጸን​ታ​ችሁ ቁሙ፤ እንደ ገናም በባ​ር​ነት ቀን​በር አት​ኑሩ።


ነገር ግን ወንጌልን አደራ ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔር የታመንን ሆነን እንዳገኘን መጠን፥ እንዲሁ እንናገራለን፤ ልባችንን የሚመረምር እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን ደስ እንደምናሰኝ አይደለም።


ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛልና፤ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤ ቄርቂስም ወደ ገላትያ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል።


በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዕውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርስዋ ተጠላልፈው የተሸነፉ ቢሆኑ፥ ከፊተኛው ኑሮአቸው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ሆኖባቸዋል።