ወንድሞች ሆይ፥ እኔም በጎ ምግባርን ሁሉ እንደምትፈጽሙ እታመንባችኋለሁ፤ እናንተ ፍጹም ዕውቀትን የተመላችሁ ናችሁ፤ ባልንጀሮቻችሁንም ልታስተምሩአቸው ትችላላችሁ።
2 ተሰሎንቄ 3:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምናዛችሁንም አሁን እንድታደርጉ ወደ ፊትም ደግሞ እንድታደርጉ ስለ እናንተ በጌታ ታምነናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ ያዘዝናችሁን አሁን አደረጋችሁ፤ ወደ ፊትም እንደምታደርጉ በጌታ እንታመናለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምናዛችሁን ነገሮች አሁንም ወደፊትም ደግሞ እንደምታደርጉ ስለ እናንተ በጌታ እንመካባችኋለን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምናዛችሁን አሁንም ሆነ ወደፊት እንደምትፈጽሙት በጌታ እንተማመንባችኋለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምናዛችሁንም አሁን እንድታደርጉ ወደ ፊትም ደግሞ እንድታደርጉ ስለ እናንተ በጌታ ታምነናል። |
ወንድሞች ሆይ፥ እኔም በጎ ምግባርን ሁሉ እንደምትፈጽሙ እታመንባችኋለሁ፤ እናንተ ፍጹም ዕውቀትን የተመላችሁ ናችሁ፤ ባልንጀሮቻችሁንም ልታስተምሩአቸው ትችላላችሁ።
በበጎ ምግባር ጸንተው ለሚታገሡ፥ ምስጋናና ክብርን፥ የማይጠፋ ሕይወትንም ለሚሹ እርሱ የዘለዓለም ሕይወትን ይሰጣቸዋል።
ራሱን እንደ ነቢይ አድርጎ ወይም መንፈስ ቅዱስ እንዳደረበት አድርጎ የሚቈጥር ቢኖር፥ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነውና ይህን የጻፍሁላችሁን ይወቅ።
የእኔ ደስታ የሁላችሁ እንደ ሆነ በሁላችሁ አምኛለሁና በመጣሁ ጊዜ ደስ ሊያሰኙኝ ከሚገባቸው ኀዘን እንዳያገኘኝ ይህን ጻፍሁላችሁ።
በብዙ የፈተንነውንና በሁሉም ነገር ትጉህ ሆኖ ያገኘነውን አሁንም በእናንተ እጅግ ስለሚታመን ከፊት ይልቅ እጅግ ትጉ የሚሆነውን ወንድማችንን ከእነርሱ ጋር እንልካለን።
እኔ ሌላ እንዳታስቡ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምኛችሁ ነበር፤ የሚያውካችሁ ግን የሆነው ቢሆን ፍዳውን ይሸከማል።
እርሱ የጀመረላችሁን በጎውን ሥራ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከሚመጣበት ቀን ድረስ እርሱ እንደሚፈጽምላችሁ አምናለሁ።
አሁንም ወንድሞች ሆይ፥ ዘወትር እንደምትሰሙኝ ሳለሁ ብቻ ሳይሆን፥ ሳልኖርም በፍርሀትና በመንቀጥቀጥ ሆናችሁ ለድኅነታችሁ ሥሩ።
እንዲሁ በመቄዶንያ ሁሉ ላሉት ወንድሞች ሁሉ ታደርጋላችሁና። ነገ ግን ወንድሞች ሆይ!ከፊት ይልቅ ልትበዙ፥ በጸጥታም ትኖሩ ዘንድ ልትቀኑ፥ የራሳችሁንም ጉዳይ ልትጠነቅቁ፥ እንዳዘዝናችሁም በውጭ ባሉት ዘንድ በአገባብ እንድትመላለሱ፥ አንዳችም እንዳያስፈልጋችሁ በእጃችሁ ልትሠሩ እንለምናችኋለን።
ወንድሞች ሆይ! ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዐት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።