ሲባም ንጉሡን፥ “ጌታዬ ንጉሡ አገልጋዩን እንዳዘዘ እንዲሁ አገልጋይህ ያደርጋል” አለው። ሜምፌቡስቴም ከንጉሡ ልጆች እንደ አንዱ ከዳዊት ገበታ ይበላ ነበር።
2 ሳሙኤል 9:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሜምፌቡስቴም ሚካ የተባለ ታናሽ ልጅ ነበረው፤ በሲባም ቤት ያሉ ሁሉ ለሜምፌቡስቴ ያገለግሉ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሜምፊቦስቴ ሚካ የተባለ አንድ ትንሽ ልጅ ነበረው፤ የሲባ ቤተ ሰዎች በሙሉ ሜምፊቦስቴን ያገለግሉት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መፊቦሼት ሚካ የተባለ አንድ ትንሽ ልጅ ነበረው፤ የጺባ ቤተሰቦች በሙሉ መፊቦሼትን ያገለግሉት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መፊቦሼት ሚካ የተባለ ወጣት ልጅ ነበረው፤ የጺባ ቤተሰብ አባሎች በሙሉ የመፊቦሼት አገልጋዮች ሆኑ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሜምፊቦስቴም ሚካ የተባለ ታናሽ ልጅ ነበረው። በሲባም ቤት ያሉ ሁሉ ለሜምፊቦስቴ ያገለግሉ ነበር። |
ሲባም ንጉሡን፥ “ጌታዬ ንጉሡ አገልጋዩን እንዳዘዘ እንዲሁ አገልጋይህ ያደርጋል” አለው። ሜምፌቡስቴም ከንጉሡ ልጆች እንደ አንዱ ከዳዊት ገበታ ይበላ ነበር።
በጸሎትም ጊዜ ምስጋናን የሚጀምሩ አለቃው የአሳፍ ልጅ፥ የዛብዲ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ማታንያ፥ በወንድሞቹም መካከል ሁለተኛ የነበረ ቦቂቦቅያ፥ የኢዶትም ልጅ፥ የጌላል ልጅ፥ የሰሙዓ ልጅ አብድያ።