ዳዊትም ለሱባን ንጉሥ ለአድርአዛር አገልጋዮች የነበሩትን ጋሻ አግሬዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው። እነዚህንም የግብፅ ንጉሥ ሱስቀም በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ዘመን ወደ ኢየሩሳሌም በወጣ ጊዜ ወሰዳቸው።
2 ሳሙኤል 8:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ዳዊት ከሶቤቅና ከተመረጡት ከአድርአዛር ከተሞች እጅግ ብዙ ናስን ወሰደ። በእርሱም ሰሎሞን የብረት ባሕርና ምሰሶዎችን፥ ሰኖችንና ሌሎች ዕቃዎችን ሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ ዳዊት ቤጣህና ቤሮታይ ከተባሉ ከአድርአዛር ከተሞችም እጅግ ብዙ ናስ አጋዘ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡ ዳዊት ቤጣህና ቤሮታይ ከተባሉ ከሀዳድዔዜር ከተሞችም እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ንጉሥ ዳዊት ሀዳድዔዜር ከሚያስተዳድራቸው ቤጣሕና ቤሮታይ ተብለው ከሚጠሩት ከተሞች እጅግ ብዙ የሆነ ነሐስ ወሰደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ዳዊት ከአድርአዛር ከተሞች ከቤጣሕና ከቤሮታይ እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ። |
ዳዊትም ለሱባን ንጉሥ ለአድርአዛር አገልጋዮች የነበሩትን ጋሻ አግሬዎች ወሰደ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው። እነዚህንም የግብፅ ንጉሥ ሱስቀም በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም ዘመን ወደ ኢየሩሳሌም በወጣ ጊዜ ወሰዳቸው።
እግዚአብሔርም ደግሞ ከጌታው ከሱባ ንጉሥ ከአድርአዛር የኰበለለውን የኤልያዳን ልጅ ሬዞንን ጠላት አድርጎ አስነሣበት።
ከዚህም በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን መታ፤ አዋረዳቸውም፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ጌትንና መንደሮችዋን ወሰደ።
ከሚጢብሐትና ከተመረጡት ከአድርአዛር ከተሞች ዳዊት እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ፤ ከዚህም ሰሎሞን የናሱን ኩሬና ዓምዶች የናሱንም ዕቃ ሠራ።
አሁንም፥ እነሆ፥ በድህነቴ ለእግዚአብሔር ቤት መቶ ሺህ መክሊት ወርቅና አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፥ ሚዛንም የሌላቸው ብዙ ናስና ብረት አዘጋጅቻለሁ፤ ደግሞም የማይቈጠር ብዙ የዝግባ እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጅቻለሁ፤ አንተም ልጄ ከዚያ በላይ ጨምር።
ለእግዚአብሔርም ቤት ሥራ አምስት ሺህ መክሊት ወርቅና ዐሥር ሺህ ዳሪክ፥ ዐሥር ሺህም መክሊት ብር፥ ዐሥራ ስምንት ሺህም መክሊት ናስ፥ መቶ ሺህም መክሊት ብረት ሰጡ።
ሐማት፥ ቤሮታ፥ በደማስቆ ድንበርና በሐማት ድንበር መካከል ያለው ሲብራይም፥ በሐውራን ድንበር አጠገብ ያለው ሐጸርሃቲኮን።