ናታንም ዳዊትን አለው፥ “ይህን ያደረገ ያ ሰው አንተ ነህ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ልትሆን ቀባሁህ፤ ከሳኦልም እጅ አዳንሁህ፤
2 ሳሙኤል 7:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም ዳዊትን ባሪያዬን እንዲህ በለው፦ ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ ወሰድሁህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሁንም ባሪያዬ ዳዊትን እንዲህ በለው፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዥ እንድትሆን ከሜዳ አነሣሁህ፤ ከበግ ጥበቃም ወሰድሁህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፤ ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፤ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዥ እንድትሆን ከሜዳ አነሣሁህ፤ ከበግ ጥበቃም ወሰድሁህ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህም ለአገልጋዬ ለዳዊት የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ ‘እኔ አንተን የበግ መንጋ ከምትጠብቅበት መስክ አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግኹህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም ዳዊትን ባሪያዬን እንዲህ በለው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አንተ መንጋውን ስትከተል በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ ወሰድሁህ፥ |
ናታንም ዳዊትን አለው፥ “ይህን ያደረገ ያ ሰው አንተ ነህ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ልትሆን ቀባሁህ፤ ከሳኦልም እጅ አዳንሁህ፤
ሴቲቱም አለች፥ “በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ እንዲህ ያለ ነገር ስለምን አሰብህ? ወይስ ንጉሥ ያሳደደውን ስላላስመለሰ እንደ በደል ከንጉሥ አፍ ይህ ቃል ወጥቶአልን?
የዳዊትም የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው። እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደረገው፥ የያዕቆብም አምላክ የቀባው፥ የታማኙ ሰው፥ በእስራኤል ዘንድ መልካም ባለመዝሙር የሆነው፥ የታማኙ የእሴይ ልጅ የዳዊት ንግግር ይህ ነው፤
ዳዊትም ሕዝቡን የሚመታውን መልአክ ባየ ጊዜ እግዚአብሔርን፥ “እነሆ፥ እኔ በድያለሁ፤ ክፉም ሥራ እኔ አድርጌአለሁ፤ እነዚህ በጎች ግን ምን አደረጉ? እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሆን ዘንድ እለምንሃለሁ” ብሎ ተናገረው።
አስቀድሞ ሳኦል በእኛ ላይ ንጉሥ ሆኖ ሳለ እስራኤልን የምታወጣና የምታገባ አንተ ነበርህ፤ እግዚአብሔርም፦ አንተ ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፤ በእስራኤልም ላይ አለቃ ትሆናለህ ብሎህ” ነበር።
ዳዊትም ሜልኮልን፥ “በእግዚአብሔር ፊት ዘምሬአለሁ፤ በእግዚአብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ከአባትሽና ከቤቱ ሁሉ ይልቅ የመረጠኝ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ፊት እጫወታለሁ፤ እዘምራለሁም፤
ሰሎሞንም አለ፥ “እርሱ በፊትህ በእውነትና በጽድቅ፥ በልብም ቅንነት ከአንተ ጋር እንደ ሄደ፥ ከአባቴ ከባሪያህ ከዳዊት ጋር ታላቅ ቸርነት አድርገሃል፤ ዛሬ እንደ ሆነም በዙፋኑ ላይ የሚቀመጥ ልጅ ሰጥተህ ታላቁን ቸርነትህን አቈይተህለታል።
ሕዝቤን እስራኤልን ከግብፅ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ ስሜ በዚያ ይሆን ዘንድ በእርስዋም ቤት ይሠራልኝ ዘንድ፥ ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ከተማን አልመረጥሁም፤ አሁን ግን ስሜ በዚያ ይሆን ዘንድ ኢየሩሳሌምን መርጫለሁ፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ይሆን ዘንድ ዳዊትን መርጫለሁ።”
አሁንም አገልጋዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አንተ መንጋውን ስትከተል በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ መርጬ ወሰድሁህ።
ዳዊትም እግዚአብሔርን፥ “ሕዝቡ ይቈጠር ዘንድ ያዘዝሁ እኔ አይደለሁምን? የበደልሁና ክፉ የሠራሁ እኔ ነኝ፤ እነዚህ በጎች ግን ምን አድርገዋል? አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን፤ ነገር ግን አቤቱ በሕዝብህ ላይ ለጥፋት አትሁን” አለው።
ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በራሱ ላይ አፈሰሰው፤ ሳመውም፤ እንዲህም አለው፥ “በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ትነግሥ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶሃል፤ የእግዚአብሔርንም ሕዝብ ትገዛለህ፤ በዙሪያውም ካሉ ጠላቶቻቸው እጅ ታድናቸዋለህ። እግዚአብሔርም በርስቱ ላይ ትነግሥ ዘንድ እንደ ቀባህ ምልክቱ ይህ ነው።
ችግረኛውን ከመሬት ያነሣዋል፤ ምስኪኑንም ከጕድፍ ያነሣዋል፤ ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጠው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሰው ዘንድ።
እንዲህም አለው፥ “ነገ በዚህች ሰዓት ከብንያም ሀገር አንድ ሰው እልክልሃለሁ፤ ልቅሶአቸው ወደ እኔ ስለ ደረሰ የሕዝቤን ሥቃያቸውን ተመልክችአለሁና ለሕዝቤ ለእስራኤል አለቃ ይሆን ዘንድ ትቀባዋለህ፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ሕዝቤን ያድናል።”