Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 17:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አሁ​ንም አገ​ል​ጋ​ዬን ዳዊ​ትን እን​ዲህ በለው፦ ሁሉን ቻይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አንተ መን​ጋ​ውን ስት​ከ​ተል በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ መርጬ ወሰ​ድ​ሁህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “አሁንም ባሪያዬ ዳዊትን እንዲህ በለው፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዥ እንድትሆን ከሜዳ አነሣሁህ፤ ከበግ ጥበቃም ወሰድሁህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አሁንም ባርያዬን ዳዊትን እንዲህ በለው፦ ‘የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ እንድትሆን አንተን ከማሰማርያው፥ ከበግ እረኝነት ወሰድሁህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “ስለዚህ እኔ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ለአገልጋዬ ለዳዊት የምለውን እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‘ከበግ እረኝነት አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግኹህ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አሁንም ባሪያዬን ዳዊትን እንዲህ በለው ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “አንተ መንጋውን ስትከተል በሕዝቤ በእስራኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ ወሰድሁህ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 17:7
13 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትም ሜል​ኮ​ልን፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዘም​ሬ​አ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ከአ​ባ​ት​ሽና ከቤቱ ሁሉ ይልቅ የመ​ረ​ጠኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ይሁን፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጫ​ወ​ታ​ለሁ፤ እዘ​ም​ራ​ለ​ሁም፤


አሁ​ንም ዳዊ​ትን ባሪ​ያ​ዬን እን​ዲህ በለው፦ ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ ትሆን ዘንድ ከበግ ጥበቃ ወሰ​ድ​ሁህ፤


ከእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ጋር ባለ​ፍ​ሁ​በት ስፍራ ሁሉ፥ ስለ ምን ቤትን ከዝ​ግባ እን​ጨት አል​ሠ​ራ​ች​ሁ​ል​ኝም? ብዬ ሕዝ​ቤን ይጠ​ብቅ ዘንድ ከእ​ስ​ራ​ኤል ፈራ​ጆች ላዘ​ዝ​ሁት ለአ​ንዱ በውኑ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁን?


በሄ​ድ​ህ​በ​ትም ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ነበ​ርሁ፥ ጠላ​ቶ​ች​ህ​ንም ሁሉ ከፊ​ትህ አጠ​ፋሁ፤ በም​ድ​ርም ላይ እን​ዳሉ እንደ ታላ​ላ​ቆች ስም ለአ​ንተ ስምን አደ​ረ​ግሁ።


ነገር ግን ስሜ በዚያ እን​ዲ​ጠ​ራ​ባት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መር​ጫ​ለሁ። በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ እን​ዲ​ሆን ዳዊ​ትን መር​ጫ​ለሁ ብሎ​አል።


እን​ዲ​ሁም የስ​ም​ዖን ባል​ን​ጀ​ራ​ዎች የነ​በሩ የዘ​ብ​ዴ​ዎስ ልጆች ያዕ​ቆ​ብና ዮሐ​ንስ ተደ​ነቁ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ስም​ዖ​ንን፥ “አት​ፍራ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህስ ሰውን ታጠ​ም​ዳ​ለህ” አለው።


ዳዊ​ትም የአ​ባ​ቱን በጎች ለመ​ጠ​በቅ ከሳ​ኦል ዘንድ ወደ ቤተ ልሔም ይመ​ላ​ለስ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos