እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ ክፉ ነገርም ቢያደርግ፥ በሰዎች በትርና በሰው ልጆች አለንጋ እገሥጸዋለሁ፤
2 ሳሙኤል 7:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፊቴም ከጣልሁት ከሳኦል ቤት እንዳራቅሁ ምሕረቴን ከእርሱ አላርቅም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምሕረቴን ከአንተ በፊት ካስወገድሁት ከሳኦል እንዳራቅሁ ሁሉ ከርሱ አላርቅም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአንተ በፊት ካስወገድሁት ከሳኦል ምሕረቴን እንዳራቅሁ ከእርሱ ግን አላርቅም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ በእርሱ ቦታ አንተ ትነግሥ ዘንድ ባስወገድኩት በሳኦል ላይ እንዳደረግሁ ዘለዓለማዊ ፍቅሬን ከልጅህ አላርቅም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፊቴም ከጣልሁት ከሳኦል እንዳራቅሁ ምሕረቴን ከእርሱ አላርቅም። |
እኔም አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ ክፉ ነገርም ቢያደርግ፥ በሰዎች በትርና በሰው ልጆች አለንጋ እገሥጸዋለሁ፤
ነገር ግን ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊትና ስለ መረጥኋት ሀገሬ ስለ ኢየሩሳሌም ለልጅህ አንድ ነገድ እሰጣለሁ እንጂ መንግሥቱን ሁሉ አልከፍልም።”
ስሙኝ፤ ጎዳናዬን ተከተሉ፤ አድምጡኝም፤ ሰውነታችሁም በበረከት ትኖራለች፤ የታመነችዪቱን የዳዊትን ምሕረት፥ የዘለዓለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።
ለአለቆች ሰላምን ለእርሱም ሕይወትን አመጣለሁና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ ግዛቱ ታላቅ ይሆናል፤ በዳዊት ዙፋን መንግሥቱ ትጸናለች፤ ለሰላሙም ፍጻሜ የለውም። የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዐት ይህን ያደርጋል።
ኀጢኣት እንደ ምዋርተኝነት ናትና አምልኮተ ጣዖትም ደዌንና ኀዘንን ያመጣል። የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ” አለው።
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና፥ እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃልና ከአንተ ጋር አልመለስም” አለው።
ሳሙኤልም፥ “እግዚአብሔር ከእስራኤል መንግሥትህን ዛሬ ከእጅህ ቀደዳት፤ ከአንተም ለሚሻል ለባልንጀራህ አሳልፎ ሰጣት፤
ልብሱንም አወለቀ፤ በፊታቸውም ትንቢት ተናገረ፤ ራቁቱንም ወድቆ በዚያ ቀን ሁሉ በዚያም ሌሊት ሁሉ ተጋደመ። ስለዚህ፥ “ሳኦል ደግሞ ከነቢያት መካከል ነውን?” ይባባሉ ነበር።