2 ሳሙኤል 6:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ በዜማ መሣሪያዎች በበገናና በመሰንቆ፥ በከበሮና በነጋሪት፥ በጸናጽልና በዕንዚራ በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይጫወቱ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትና የእስራኤል ቤት በሙሉ በዝማሬ፣ በበገና፣ በመሰንቆ፣ በከበሮ፣ በጸናጽልና በቃጭል ባለ ኀይላቸው ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ያሸበሽቡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትና የእስራኤል ቤት በሙሉ በዝማሬ፥ በበገና፥ በመሰንቆ፥ በከበሮ፥ በጽናጽልና በቃጭል ድምፅ በጌታ ፊት ያሸበሽቡ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ የበገና፥ የመሰንቆ፥ የከበሮ፥ የጸናጽልና የቃጭል ድምፅ እያሰሙ ለእግዚአብሔር ክብር በመዘመር በሙሉ ኀይላቸው ያሸበሽቡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትና የእስራኤልም ቤት ሁሉ በቅኔና በበገና በመሰንቆም በከበሮም በነጋሪትና በጸናጽል በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኃይላቸው ይጫወቱ ነበር። |
ዳዊትና እስራኤል ሁሉ ከመዘምራን ጋር በበገና፥ በመሰንቆና በከበሮ፥ በጸናጽልና በመለከት በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኀይላቸው ይዘምሩ ነበር።
እንዲሁ እስራኤል ሁሉ በይባቤ፥ ቀንደ መለከትና እንቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽልና መሰንቆም፥ በገናም እየመቱ፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።
ከበገናው ድምፅ ጋር አስተባብረው ለሚያጨበጭቡ ሰዎች፤ ይኸውም የማያልፍ ለሚመስላቸውና እንደሚያመልጣቸው ለማያውቁ፤
ከዚያም በኋላ የፍልስጥኤማውያን ጭፍራ ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ኮረብታ ትመጣለህ፤ በዚያም ፍልስጥኤማዊው ናሴብ አለ፤ ወደዚያም ወደ ከተማዪቱ በደረስህ ጊዜ በገናና ከበሮ፥ እምቢልታና መሰንቆ ይዘው ትንቢት እየተናገሩ ከኰረብታው መስገጃ የሚወርዱ የነቢያትን ጉባኤ ታገኛለህ።
አገልጋዮችህ በፊትህ ይናገሩ፤ በበገና የሚዘምር ሰውም ለጌታቸው ይፈልጉለት፤ ክፉ መንፈስም በመጣብህ ጊዜ በገናውን ሲመታ አንተ ደኅና ትሆናለህ፤ እርሱም ያሳርፍሃል” አሉት።