አማልክቶቻቸውንም በእሳት አቃጥለዋል፤ የእንጨትና የድንጋይ የሰው እጅ ሥራም ነበሩ እንጂ አማልክት አልነበሩምና ስለዚህ አጥፍተዋቸዋል።
2 ሳሙኤል 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጣዖቶቻቸውንም በዚያ ተዉ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ወሰዱአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያንም ጣዖቶቻቸውን ትተው ሸሽተው ስለ ነበር፣ ዳዊትና ሰዎቹ ወስደው አቃጠሏቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍልስጥኤማውያንም ጣዖቶቻቸውን ትተው ሸሹ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ወሰዱአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያን በሸሹ ጊዜ ጣዖቶቻቸውን ጥለው ሄዱ፤ ዳዊትና ተከታዮቹም ማርከው ወሰዱአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጣዖቶቻቸውንም በዚያ ተዉ፥ ዳዊትና ሰዎቹም ወሰዱአቸው። |
አማልክቶቻቸውንም በእሳት አቃጥለዋል፤ የእንጨትና የድንጋይ የሰው እጅ ሥራም ነበሩ እንጂ አማልክት አልነበሩምና ስለዚህ አጥፍተዋቸዋል።
በግብፅም አማልክት ቤቶች እሳትን ያነድዳል፤ ያቃጥላቸውማል፤ ይማርካቸውማል፤ እረኛም ልብሱን እንደሚቀምል እንዲሁ የግብፅን ሀገር ይቀምላታል፤ ከዚያም በሰላም ይወጣል።
በሥራሽና በመዝገብሽ ታምነሻልና አንቺ ደግሞ ትያዢያለሽ፤ ካሞሽም ከካህናቱና ከአለቆቹ ጋር በአንድነት ይማረካል።
የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ ከእነርሱም የተሠራባቸውን ብርንና ወርቅን፥ አትመኝ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትበድልበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።
ነገር ግን እንዲህ አድርጉባቸው፤ መሠዊያቸውን አፍርሱ፤ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም ቍረጡ፥ የአማልክቶቻቸውንም ምስል በእሳት አቃጥሉ።