ንጉሡ ዳዊትም ወደ በውሪም መጣ፤ እነሆም፥ ሳሚ የሚባል የጌራ ልጅ ከሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ከዚያ ወጣ፤ እየሄደም ይረግመው ነበር።
2 ሳሙኤል 3:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባልዋም እያለቀሰ ከእርስዋ ጋር ሄደ፤ እስከ ብራቂም ድረስ ተከተላት። አበኔርም፥ “ሂድ፤ ተመለስ” አለው፤ እርሱም ተመለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሏም እስከ ባሑሪም ከተማ ድረስ እያለቀሰ ተከትሏት ሄደ፤ ከዚያም አበኔር፣ “በል ይበቃል! ወደ ቤትህ ተመለስ” አለው። ስለዚህም ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባሏም እስከ ባሑሪም ከተማ ድረስ እያለቀሰ ተከትሎአት ሄደ፤ ከዚያም አበኔር፥ “ሂድ፥ ተመለስ” አለው፤ እርሱም ተመለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባልዋ ፓልጢኤልም እያለቀሰ እስከ ባሑሪም ከተማ ድረስ ተከተላት፤ ነገር ግን አበኔር “ወደ ቤትህ ተመለስ” ባለው ጊዜ ተመለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባልዋም እያለቀሰ ከእርስዋ ጋር ሄደ፥ እስከ ብራቂም ድረስ ተከተላት። አበኔርም፦ ሂድ፥ ተመለስ አለው፥ እርሱም ተመለሰ። |
ንጉሡ ዳዊትም ወደ በውሪም መጣ፤ እነሆም፥ ሳሚ የሚባል የጌራ ልጅ ከሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ከዚያ ወጣ፤ እየሄደም ይረግመው ነበር።
አንድ ብላቴናም አይቶ ለአቤሴሎም ነገረው፤ እነርሱ ግን ፈጥነው ሄዱ፤ ወደ ባውሪምም ወደ አንድ ሰው ቤት መጡ፤ በግቢውም ውስጥ ጕድጓድ ነበረው፤ ወደዚያም ውስጥ ወረዱ፤
ከእርሱም ጋራ ከብንያም ወገን የሆኑ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ የሳኦልም ቤት አገልጋይ ሲባ ከእርሱም ጋር ዐሥራ አምስቱ ልጆቹና ሃያው አገልጋዮቹ ነበሩ፤ በንጉሡም ፊት በቀጥታ ወደ ዮርዳኖስ ሄዱ።
የባውሬም ሀገር ሰው የብንያማዊው የጌራ ልጅ ሳሚ እነሆ! በአንተ ዘንድ ነው፤ እኔም ወደ መሃናይም በሄድሁ ጊዜ ብርቱ ርግማን ረገመኝ፤ ከዚያም በኋላ ዮርዳኖስን በተሻገርሁ ጊዜ ሊቀበለኝ ወረደ፤ እኔም፦ ‘በሰይፍ አልገድልህም’ ብዬ በእግዚአብሔር ምየለታለሁ።
የናታንያም ልጅ እስማኤል ከመሴፋ ወጥቶ እያለቀሰ ሊገናኛቸው ሄደ፤ በተገናኛቸውም ጊዜ፥ “ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ኑ” አላቸው።