2 ሳሙኤል 24:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሥ ሆይ፥ ኦርና ይህን ሁሉ ለንጉሡ ይሰጣል” አለው፤ ኦርናም ንጉሡን፥ “አምላክህ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ሆይ፣ ይህን ሁሉ ኦርና ለንጉሡ ይሰጣል።” እንዲሁም ኦርና፣ “እግዚአብሔር አምላክህ ይቀበልህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሥ ሆይ፥ ይህን ሁሉ ኦርና ለንጉሡ ይሰጣል።” እንዲሁም ኦርና፥ “ጌታ አምላክህ ይቀበልህ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኦርናም “ይህን ሁሉ ለንጉሡ ሰጥቶ እግዚአብሔር መሥዋዕትህን ይቀበልልህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሥ ሆይ፥ ይህን ሁሉ ኦርና ለንጉሡ ይሰጣል አለው፥ ኦርናም ንጉሡን፦ አምላክህ እግዚአብሔር ይቀበልህ አለው። |
የቄዳር በጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ፤ የነባዮትም አውራ በጎች ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ በመሠዊያዬ ላይም የተመረጠው መሥዋዕት ይቀርባል፤ የጸሎቴ ቤትም ይከብራል።
መሥዋዕትንም ቢሠዉ፥ ሥጋንም ቢበሉ፤ እግዚአብሔር አይቀበላቸውም፤ አሁንም በደላቸውን ያስባል፤ በኀጢአታቸውም ይበቀላቸዋል፤ እነርሱም ወደ ግብፅ ይመለሳሉ፤ በአሦርም ርኩስ ነገርን ይበላሉ።
እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።