በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት፤ ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።
2 ሳሙኤል 24:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “ውጣ፤ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን ጋድ ወደ ዳዊት ዘንድ ሄዶ፣ “ውጣና በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ላይ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ቀን ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “ውጣና በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ላይ ለጌታ መሠዊያ ሥራ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያው ዕለት ነቢዩ ጋድ ወደ ዳዊት ሄዶ “ወደ ኦርና አውድማ ሄደህ ለእግዚአብሔር መሠዊያውን ሥራ!” አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ፦ ውጣ፥ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ አለው። |
በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት፤ ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።
ሰሎሞንም እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በአሞሪያ ተራራ ዳዊት ባዘጋጀው ስፍራ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ።
ደሙንም ከአፉ ውስጥ ርኩሱንም ነገር ከጥርሱ መካከል አስወግዳለሁ፣ እርሱም ደግሞ ለአምላካችን ቅሬታ ይሆናል፣ በይሁዳም እንደ አለቃ ይሆናል፥ አቃሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል።