እነሆም፥ ኩሲ መጣ፤ ኩሲም፥ “እግዚአብሔር በላይህ የተነሡትን ሁሉ ዛሬ እንደ ተበቀለልህ ለጌታዬ ለንጉሡ ወሬ አምጥቻለሁ” አለ።
2 ሳሙኤል 22:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጠላቶቼ የሚያወጣኝ እርሱ ነው፤ በእኔም ላይ ከቆሙ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፤ ከግፈኛም ሰው ታድነኛለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ከጠላቶቼ እጅ ነጻ ያወጣኛል። አንተ ከጠላቶቼ በላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤ ከጨካኝ ሰዎችም እጅ ታደግኸኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጠላቶቼ እጅ ነጻ የሚያወጣኝ እርሱ ነው። በጠላቶቼ ላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤ ከጨካኝ ሰዎችም እጅ ታደግኸኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጠላቶቼም ታድነኛለህ። በጠላቶቼ ላይ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፤ ከግፈኞችም ታድነኛለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጠላቶቼ የሚያወጣኝ እርሱ ነው፥ በእኔም ላይ ከቆሙ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፥ ከግፈኛ ሰው ታድነኛለህ። |
እነሆም፥ ኩሲ መጣ፤ ኩሲም፥ “እግዚአብሔር በላይህ የተነሡትን ሁሉ ዛሬ እንደ ተበቀለልህ ለጌታዬ ለንጉሡ ወሬ አምጥቻለሁ” አለ።
ዳዊትም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ እንዳዘጋጀው፥ ስለ ሕዝቡ ስለ እስራኤልም መንግሥቱን ከፍ እንዳደረገ ዐወቀ።
ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥ ዐመፃን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ለኀጢአት ምክንያት እንዳልሰጥ፤ ከምርጦቻቸውም ጋር አልተባበር።
ችግረኛውን ከመሬት ያነሣዋል፤ ምስኪኑንም ከጕድፍ ያነሣዋል፤ ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጠው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሰው ዘንድ።