የሳዶቅ ልጅ አኪማሖስ ግን፥ “እግዚአብሔር ከጠላቶቹ እጅ እንደ ፈረደለት ፈጥኜ ሄጄ ለንጉሥ የምሥራች ልንገርን?” አለ።
2 ሳሙኤል 22:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቀሌን የሚመልስልኝ አምላክ ጽኑዕ ነው። አሕዛብን በበታቼ ያስገዛልኛል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቀሌን የሚመልስልኝ፣ አሕዛብንም ከሥሬ የሚያስገዛልኝ እርሱ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚበቀልልኝ አምላክ፥ ሕዝቦችን ከሥሬ የሚያስገዛልኝ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ጠላቶቼን ይበቀልልኛል፤ ሕዝቦችንም ከበታቼ አድርጎ ያስገዛልኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቀሌን የሚመልስልኝ አምላክ፥ አሕዛብን በበታቼ የሚያስገዛ፥ |
የሳዶቅ ልጅ አኪማሖስ ግን፥ “እግዚአብሔር ከጠላቶቹ እጅ እንደ ፈረደለት ፈጥኜ ሄጄ ለንጉሥ የምሥራች ልንገርን?” አለ።
እነሆም፥ ኩሲ መጣ፤ ኩሲም፥ “እግዚአብሔር በላይህ የተነሡትን ሁሉ ዛሬ እንደ ተበቀለልህ ለጌታዬ ለንጉሡ ወሬ አምጥቻለሁ” አለ።
የኢያቡስቴንም ራስ ይዘው ወደ ዳዊት ወደ ኬብሮን መጡ፤ ንጉሡንም፥ “ነፍስህን ይሻ የነበረው የጠላትህ የሳኦል ልጅ የኢያቡስቴ ራስ እነሆ፤ እግዚአብሔርም ዛሬ ከጠላትህ ከሳኦልና ከዘሩ ለጌታችን ለንጉሥ በቀሉን መለሰለት” አሉት።
በፍርድ ቀን እበቀላቸዋለሁ፤ እግራቸው በሚሰናከልበት ጊዜ፥ የጥፋታቸው ቀን ቀርቦአልና፥ የተዘጋጀላችሁም ፈጥኖ ይደርስባችኋልና።
እነሆ፥ የልብስህ ዘርፍ በእጄ እንዳለ ተመልክተህ ዕወቅ፤ የልብስህንም ዘርፍ በቈረጥሁ ጊዜ አልገደልሁህም፤ ስለዚህም በእጄ ክፋት፥ በደልና ክዳት እንደሌለ፥ አንተንም እንዳልበደልሁህ ዕወቅ፤ አንተ ግን ነፍሴን ልታጠፋ ታጠምዳለህ።
እንዲህም ይሆናል፤ እግዚአብሔር ለጌታዬ የተናገረውን ቸርነት ሁሉ ያደርግልሃል፤ በእስራኤልም ላይ አለቃ አድርጎ ይሾምሃል፤
ዳዊትም ናባል እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ፥ “ከናባል እጅ የስድቤን ፍርድ የፈረደልኝ፥ ባሪያውንም ከክፉዎች እጅ የጠበቀ እግዚአብሔር ይመስገን፤ እግዚአብሔርም የናባልን ክፋት በራሱ ላይ መለሰ” አለ። ዳዊትም ያገባት ዘንድ አቤግያን እንዲያነጋግሩለት ላከ።