2 ሳሙኤል 22:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባዕድ ልጆች ዋሹኝ፤ በጆሮ ሰምተው መለሱልኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባዕድ አገር ሰዎች ይፈሩኛል፤ እንደ ሰሙኝም ወዲያውኑ ይታዘዙኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባዕዳን ሊለማመጡኝ መጡ፤ እንደ ሰሙኝም በፍጥነት ይታዘዙኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባዕዳን ያጐነብሱልኛል፤ ዝናዬን እንደ ሰሙም ይገዙልኛል መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባዕድ ልጆች ደለሉኝ፥ በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ። |
ወደ እግዚአብሔርም የተጠጋ መጻተኛ፥ “በእውነት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ይለየኛል” አይበል፤ ጃንደረባም፥ “እነሆ፥ እኔ እንደ ደረቀ ዛፍ ነኝ” አይበል።
ከሌላም ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር የተመለሱትን ለእርሱም ባሪያዎች የሆኑትን፥ የእግዚአብሔርንም ስም የወደዱትን፥ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎቹ የሆኑትን፥ “ሰንበታቴን የሚጠብቁትንና የማያረክሱትን፥ በቃል ኪዳኔም ጸንተው የሚኖሩትን ሁሉ፥
ሲሞንም ወዲያውኑ አምኖ ተጠመቀ፤ ፊልጶስንም ይከተል ጀመር፤ በፊልጶስም እጅ የሚደረገውን ተአምርና ታላቅ ኀይል ባየ ጊዜ ይደነቅ ነበር።
እስራኤል ሆይ ብፁዕ ነህ፤ በእግዚአብሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማንነው? እርሱ ያጸንሃል፤ ይረዳሃልም፤ ትምክሕትህ በሰይፍህ ነው፤ ጠላቶችህ ውሸታሞች ናቸው፤ አንተም በአንገታቸው ላይ ትጫናለህ።”