“ይሁዳ፥ ወንድሞችህ አንተን ያመሰግኑሃል፤ እጅህ በጠላቶችህ ደንደስ ላይ ነው፤ የአባትህ ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ።
2 ሳሙኤል 22:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፤ የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላቶቼ ፊታቸውን አዙረው እንዲሸሹ አደረግሃቸው። ባላንጣዎቼንም ደመሰስኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላቶቼ ከፊቴ ወደ ኋላ እንዲሸሹ አደረግህ፤ የሚጠሉኝንም ሁሉ አጠፋቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው። |
“ይሁዳ፥ ወንድሞችህ አንተን ያመሰግኑሃል፤ እጅህ በጠላቶችህ ደንደስ ላይ ነው፤ የአባትህ ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ።
በፊትህ መፈራትን እሰድዳለሁ፤ የምትሄድበትን ሕዝብ ሁሉ አስደነግጣቸዋለሁ፤ ጠላቶችህንም ሁሉ እንዲሸሹልህ አደርጋለሁ።
እነዚያንም ነገሥት ወደ ኢያሱ ባመጡአቸው ጊዜ ኢያሱ የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ ጠራ፤ ከእርሱም ጋር የሄዱትን የተዋጊዎችን አለቆች “ቅረቡ፤ በእነዚህም ነገሥት አንገት ላይ እግራችሁን አኑሩ” አላቸው። ቀረቡም በአንገታቸውም ላይ እግራቸውን አኖሩ።