2 ሳሙኤል 22:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእጆቼ ጦርነትን ያስተምራል፤ ለክንዴም የናስ ቀስት አዘዘ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናቸዋል፤ ክንዶቼም የናስ ቀስት መገተር ይችላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክንዶቼም የናስ ቀስት መሳብ እንዲችሉ፥ እጆቼን ለጦርነት ያሰለጥናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጆቼን ለጦርነት ያሠለጥናል፤ የነሐስን ቀስት መሳብ እንዲችሉ ክንዶቼን ያበረታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጆቼን ሰልፍ ያስተምራል፥ በክንዴ የናስ ቀስት እገትራለሁ። |
ከግራ እጅህም ቀስትህን አስጥልሃለሁ፤ ከቀኝ እጅህም ፍላጾችህን አስረግፍሃለሁ፤ በእስራኤልም ተራሮች ላይ እጥልሃለሁ።
ዳዊትም ፍልስጥኤማዊዉን አለው፥ “አንተ ሰይፍና ጦር፥ ጋሻም ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን ዛሬ በተገዳደርኸው በእስራኤል ጭፍሮች አምላክ ስም በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ።