ከብርቱዎች ጠላቶቼ፥ ከሚጠሉኝም አዳነኝ፤ በርትተውብኝ ነበርና።
ከብርቱ ጠላቶቼ አዳነኝ፤ ከሚበረቱብኝ ባላጋሮቼም ታደገኝ።
በርትተውብኝ ነበርና፥ ከብርቱ ጠላቶቼ፥ ከሚጠሉኝም ታደገኝ።
በጣም በርትተውብኝ ከነበሩት ከኀይለኞች ጠላቶቼና ከሚጠሉኝ ሰዎች ሁሉ እጅ እግዚአብሔር አዳነኝ።
ከብርቱዎች ጠላቶቼ፥ ከሚጠሉኝም አዳነኝ፥ በርትተውብኝ ነበርና።
ዳዊትም እግዚአብሔር ከሳኦል እጅና ከጠላቶቹ ሁሉ እጅ ባዳነው ቀን የዚህን መዝሙር ቃል ለእግዚአብሔር ተናገረ።
ከላይ ላከ፤ ወሰደኝም፤ ከብዙ ውኆችም አወጣኝ።
በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ደጋፊዬ ሆነ።
ተነሥ፥ አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፤ አንተ በከንቱ የሚጠሉኝን ሁሉ መትተሃልና፥ የኃጥኣንንም ጥርስ ሰብረሃልና።
ምሕረትህን በሚያውቁህ ላይ፥ ጽድቅህንም በልበ ቅኖች ላይ ዘርጋ።
አቤቱ፥ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥ በወገኖችም ዘንድ እዘምርልሃለሁ፤
እርሱም እንዲህ ካለ ሞት አዳነን፤ ያድነንማል፤ አሁንም እንደሚያድነን እርሱን እንታመናለን።
ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ እንዲሰሙት፥ ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፤ ከአንበሳ አፍም ዳንሁ።