የዳዊት ኀያላንም ስማቸው ይህ ነው። የኢዮአብ ወንድም አሣሄል በሠላሳው መካከል ነበረ፤ የቤተ ልሔም ሰው የአጎቱ የዱዲ ልጅ ኤልያናን፥
2 ሳሙኤል 21:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም በሮም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ሆነ፤ የቤተልሔማዊውም የዓሬኦርጌም ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው ጎዶልያን ገደለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ በተደረገ ሌላ ጦርነትም፣ የቤተ ልሔሙ የዓሬዓርጊም ልጅ ኤልያናን፣ የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን የጋት ሰው የጎልያድን ወንድም ገደለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በተደረገ ሌላ ጦርነትም፥ የቤተልሔሙ የያዒር ዓርጊምን ልጅ ኤልሐናን፥ የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን የጌት ሰው ጎልያድን ገደለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም በጎብ ሌላ ጦርነት ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተደረገ፤ በዚህም ጊዜ የቤተልሔም ተወላጅ የሆነው የያዒር ልጅ ኤልሐናን የጋት ተወላጅ የሆነውንና የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን ጎልያድ ተብሎ የሚጠራውን ሌላ ፍልስጥኤማዊ ገደለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም በጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ነበረ፥ የቤተልሔማዊውም የየዓሬኦርጊም ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው ጎልያድን ገደለ። |
የዳዊት ኀያላንም ስማቸው ይህ ነው። የኢዮአብ ወንድም አሣሄል በሠላሳው መካከል ነበረ፤ የቤተ ልሔም ሰው የአጎቱ የዱዲ ልጅ ኤልያናን፥
ደግሞም በጭፍሮቹ ዘንድ የነበሩት ኀያላን እነዚህ ናቸው፤ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፥ የቤተ ልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፤
ደግሞም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ነበረ፤ የያዔርም ልጅ ኤልያናን የጌት ሰው የጎልያድን ወንድም ለሕሜን ገደለ። የጦሩ የቦም እንደ ሸማኔ መጠቅለያ ሆኖ ተገኘ።
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? የዘይቱን ቀንድ ሞልተህ ና፤ በልጆቹ መካከል ለእኔ ንጉሥ አዘጋጅቼአለሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እልክሃለሁ” አለው።