2 ሳሙኤል 21:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ቀጥሎም በጎብ ሌላ ጦርነት ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተደረገ፤ በዚህም ጊዜ የቤተልሔም ተወላጅ የሆነው የያዒር ልጅ ኤልሐናን የጋት ተወላጅ የሆነውንና የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን ጎልያድ ተብሎ የሚጠራውን ሌላ ፍልስጥኤማዊ ገደለ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋራ በተደረገ ሌላ ጦርነትም፣ የቤተ ልሔሙ የዓሬዓርጊም ልጅ ኤልያናን፣ የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን የጋት ሰው የጎልያድን ወንድም ገደለው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በተደረገ ሌላ ጦርነትም፥ የቤተልሔሙ የያዒር ዓርጊምን ልጅ ኤልሐናን፥ የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን የጌት ሰው ጎልያድን ገደለው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ደግሞም በሮም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ሆነ፤ የቤተልሔማዊውም የዓሬኦርጌም ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው ጎዶልያን ገደለው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ደግሞም በጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ነበረ፥ የቤተልሔማዊውም የየዓሬኦርጊም ልጅ ኤልያናን የጦሩ የቦ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የነበረውን የጌት ሰው ጎልያድን ገደለ። Ver Capítulo |
ከሠላሳዎቹ መካከል የሌሎቹ ሰዎች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ የኢዮአብ ወንድም ዐሣሄል፥ የቤተልሔሙ ተወላጅ የዶዶ ልጅ ኤልሐናን፥ የሐሮድ ተወላጅ ሻሞት፥ የፌሌጥ ተወላጅ የሆነው ሔሌጽ፥ የተቆዓ ተወላጅ የሆነው የዒቄሽ ልጅ ዒራ፥ የዐናቶት ተወላጅ የሆነው አቢዔዜር፥ የሑሻ ተወላጅ የሆነው ሲበካይ፥ የአሖሕ ተወላጅ የሆነው ዒላይ፥ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው ማህራይ፥ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው የባዕና ልጅ ሔሌድ፥ በብንያም ግዛት የምትገኘው የጊብዓ ተወላጅ የሪባይ ልጅ ኢታይ፥ የፒርዓቶን ተወላጅ የሆነው በናያ፥ በጋዓሽ አጠገብ ባሉት ሸለቆዎች የተወለደው ሑራይ፥ የዓረባ ተወላጅ የሆነው አቢኤል፥ የባሕሩም ተወላጅ የሆነው ዓዝማዌት፥ የሻዓልቦን ተወላጅ የሆነው ኤልያሕባ፥ የጊዞን ተወላጅ የሆነው ሃሼም፥ የሃራር ተወላጅ የሆነው የሻጌ ልጅ ዮናታን፥ የሀራር ተወላጁ የሳካር ልጅ አሒአም፥ የኡር ልጅ ኤሊፋል፥ የመኬራ ተወላጅ የሆነው ሔፌር፥ የፐሎን ተወላጅ የሆነው አሒያ፥ የቀርሜሎስ ተወላጅ የሆነው ሔጽሮ፥ የኤዝባይ ልጅ ናዕራይ፥ የናታን ወንድም ዮኤል፥ የሃግሪ ልጅ ሚብሐር፥ የዐሞን ተወላጅ የሆነው ጼሌቅ፥ የበኤሮት ተወላጅና የኢዮአብ ጋሻጃግሬ የነበረው ናሕራይ፥ የያቲር ተወላጆች የሆኑት ዒራና ጋሬብ፥ ሒታዊው ኦርዮን፥ የአሕላይ ልጅ ዛባድ፥ የሺዛ ልጅ ዐዲና፤ (ይህ ሰው የራሱ ቡድን የሆኑ ሠላሳ ወታደሮችን እንደ ያዘ ከሮቤል ነገድ የታወቀ ነበር፤) የማዕካ ልጅ ሐናን፥ የሚታን ተወላጅ የሆነው ኢዮሣፍጥ፥ የዐሽተራ ተወላጅ የሆነው ዑዚያ፥ የዓሮዔር ተወላጅ የሆነው የሆታም ልጆች ሻማዕና ይዒኤል፥ የቲጺ ተወላጅ የሆነው የሺምሪ ልጆች ይዲዕኤልና ዮሐ፥ የማሐዋ ተወላጅ የሆነው ኤሊኤል፥ የኤልናዓም ልጆች ይሪባይና ዮሻውያ፥ የሞአብ ተወላጅ የሆነው ዩትማ፥ የጾባ ተወላጆች የሆኑት ኤሊኤል፥ ዖቤድና ያዕሲኤል።
ከሠላሳዎቹ መካከል የሌሎቹ ሰዎች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ የኢዮአብ ወንድም ዐሣሄል፤ የቤተልሔሙ ተወላጅ የዶዶ ልጅ ኤልሐናን፤ የሐሮድ ተወላጆች የሆኑት ሻማና ኤሊቃ፤ የፌሌጥ ተወላጅ የሆነው ሔሌጽ፤ የተቆዓ ተወላጅ የሆነው የዒቄሽ ልጅ ዒራ፤ የዐናቶት ተወላጅ የሆነው አቢዔዜር፤ የሑሻ ተወላጅ የሆነው መቡናይ፤ የአሖሕ ተወላጅ የሆነው ጻልሞን፤ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው ማህራይ፤ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው የባዕና ልጅ ሔሌብ፤ በብንያም ግዛት የምትገኘው የጊብዓ ተወላጅ የሆነው የሪባይ ልጅ ኢታይ፤ የፒርዓቶን ተወላጅ የሆነው በናያ፤ በጋዓሽ ሸለቆ አጠገብ የተወለደው ሂዳይ፤ የዓርባ ተወላጅ የሆነው ኢቢዓልቦን፤ የባርሑም ተወላጅ የሆነው ዓዝማዌት፤ የሻዓልቦን ተወላጅ የሆነው ኤልያሕባ፤ የያሼን ልጆች፤ ዮናትን፤ የሐራር ተወላጅ የሆነው ሻማ፤ የሐራር ተወላጅ የሆነው የሻራር ልጅ አሒአም፤ የማዕካ ተወላጅ የሆነው የአሐሰባይ ልጅ ኤሊፌሌጥ፤ የጊሎ ተወላጅ የሆነው የአኪጦፌል ልጅ ኤሊዓም፤ የቀርሜሎስ ተወላጅ የሆነው ሔጽሮ፤ የዐረብ ተወላጅ የሆነው ፓዓራይ፤ የጾባ ልጅ የሆነው የናታን ልጅ ዪግአል የጋድ ተወላጅ የሆነው ባኒ፤ የዐሞን ተወላጅ የሆነው ጼሌቅ፤ የኢዮአብ ጋሻ ጃግሬ የነበረውና የበኤሮት ተወላጅ የሆነው ናሕራይ፤ የያቲር ተወላጆች የሆኑት ዒራና ጋሬብ፤ ሒታዊው ኦርዮን። ዝነኞች የሆኑት ኀያላን ወታደሮች ጠቅላላ ድምር ሠላሳ ሰባት ነበር።