2 ሳሙኤል 20:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ቤቱ መጣ፤ ንጉሡም ቤቱን ሊጠብቁ የተዋቸውን ዐሥሩን ቁባቶች ወስዶ ለጠባቂ ሰጣቸው፤ ቀለብም ሰጣቸው፤ ነገር ግን ወደ እነርሱ አልገባም፤ በቤትም ተዘግተው እስኪሞቱ ድረስ መበለቶች ሆነው ተቀመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መንግሥቱ ተመለሰ፤ ንጉሡም ቤቱን እንዲጠብቁ ትቷቸው የሄደውን ዐሥሩን ቁባቶቹን ወሰደ፤ በአንድ ቤትም ውስጥ እንዲጠበቁ አደረገ። ቀለብ ሰጣቸው፤ ይሁን እንጂ ወደ እነርሱ አልገባም ነበር፤ እነርሱም እስከ ሞቱበት ጊዜ ድረስ መበለት ሆነው፣ ለብቻቸው ተገልለው ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መንግሥቱ በተመለሰ ጊዜ፤ ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁ ትቶአቸው የሄደውን ዐሥሩን ዕቁባቶቹን ወሰደ፤ በአንድ ቤትም ውስጥ እንዲጠበቁ አደረገ። ቀለብ ሰጣቸው፤ ይሁን እንጂ ወደ እነርሱ አልገባም ነበር፤ እነርሱም እስከሞቱበት ጊዜ ድረስ መበለት ሆነው፥ ለብቻቸው ተገልለው ተቀመጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤተ መንግሥቱ በደረሰ ጊዜ፥ ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁለት ትቶአቸው የነበሩትን ዐሥር ቊባቶቹን ወደ ሌላ ወስዶ በዘበኛ እንዲጠበቁ አደረገ፤ የሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ እንዲሰጣቸው አዘዘ፤ ይሁን እንጂ ከእነርሱ ጋር ግንኙነት አልፈጸመም፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞታቸው በቤት ተወስነው እንደ መበለቶች በመሆን ኖሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ቤቱ መጣ፥ ንጉሡም ቤቱን ሊጠብቁ የተዋቸውን አሥሩን ቁባቶች ወስዶ ለጠባቂ ሰጣቸው፥ ቀለብም ሰጣቸው፥ ነገር ግን ወደ እነርሱ አልገባም፥ በቤት ተዘግተው እስኪሞቱም ድረስ ባልቴቶች ሆነው ተቀመጡ። |
የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ ከዳዊት ተለይተው የቢኮሪ ልጅ ሳቡሄን ተከትለው ሄዱ፤ የይሁዳ ሰዎች ግን ከዮርዳኖስ ጀምረው ኢየሩሳሌም እስኪደርሱ ንጉሣቸውን ተከተሉ።