2 ሳሙኤል 2:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አበኔርም ኢዮአብን፥ “ጐልማሶቻችን ይነሡ፤ በፊታችንም ይቈራቈሱ” አለው፤ ኢዮአብም፥ “ይነሡ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አበኔር፣ ኢዮአብን፣ “ከእናንተም ከእኛም ጕልማሶች ይነሡና በፊታችን በጨበጣ ውጊያ ይጋጠሙ” አለው። ኢዮአብም፣ “ይሁን ዕሺ ይጋጠሙ” ብሎ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም አበኔር፥ ኢዮአብን፥ “ጉልማሶች ይነሡና በፊታችን ትግል ይግጠሙ” አለው። ኢዮአብም፥ “ይሁን እሺ ይግጠሙ” ብሎ መለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ አበኔር ኢዮአብን “ከእያንዳንዳችን ወገን ወጣቶችን መርጠን በጦር መሣሪያ ውጊያ በመግጠም ይወዳደሩ” አለው። ኢዮአብም “መልካም ነው” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አበኔርም ኢዮአብን፦ ጕልማሶች ይነሡ፥ በፊታችንም ይቆራቆሱ አለው፥ ኢዮአብም፦ ይነሡ አለ። |
ሁሉም እያንዳንዱ የወደረኛውን ራስ በእጁ ያዘ፤ ሰይፉንም በወደረኛው ጐን ሻጠ፤ ተያይዘውም ወደቁ። የዚያም ስፍራ ስም “በገባዖን የሸመቁ ሰዎች ድርሻ” ተብሎ ተጠራ፤
በዚያን ጊዜም አሜስያስ፥ “ና እርስ በርሳችን ፊት ለፊት እንተያይ” ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮአካዝ ልጅ ወደ ዮአስ መልእክተኞችን ላከ።