ያችም ሴት አለች፥ “መልካሙንና ክፉውን ነገር ለመስማት ንጉሡ ጌታዬ እንደ መሥዋዕትና እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነውና የጌታዬ የንጉሡ ቃል እንደዚሁ ነው፤ አምላክህም እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን።”
2 ሳሙኤል 19:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም በእኔ በባሪያህ ላይ ክፉ አደረገ፤ አንተ ጌታዬ ንጉሥ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነህ፤ በፊትህም ደስ ያሰኘህን አድርግ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጌታዬ በንጉሡ ፊትም የእኔን የባሪያህን ስም አጥፍቷል፤ መቼም ንጉሥ ጌታዬ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለ ሆንህ ደስ ያለህን ሁሉ አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እንዲህ አለው፤ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ እኔ አገልጋይህ ሽባ በመሆኔ፥ ‘ከንጉሡ ጋር መሄድ እንድችል አህያዬ ይጫንልኝና ልቀመጥበት’ ብዬ ነበር፤ ይሁን እንጂ አገልጋዬ አታለለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሆይ! እንዲያውም ስለ እኔ በውሸት ለአንተ የነገረህ ጉዳይ አለ፤ ነገር ግን አንተ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ስለ ሆንክ መልካም መስሎ የታየህን አድርግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም እኔን ባሪያህን ለጌታዬ ለንጉሡ አማ፥ አንተ ጌታዬ ንጉሥ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነህ፥ ደስም ያሰኘህን አድርግ። |
ያችም ሴት አለች፥ “መልካሙንና ክፉውን ነገር ለመስማት ንጉሡ ጌታዬ እንደ መሥዋዕትና እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነውና የጌታዬ የንጉሡ ቃል እንደዚሁ ነው፤ አምላክህም እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን።”
ይህን ነገር እናገር ዘንድ እንድመጣ ይህን ምክር ያደረገ አገልጋይህ ኢዮአብ ነው። ጌታዬ ግን በዚህ ዓለም የሚደረገውን ሁሉ ታውቅ ዘንድ እንደ መልአከ እግዚአብሔር ጥበብ ጥበበኛ ነህ፤”
ንጉሡም፥ “የጌታህ ልጅ ወዴት ነው?” አለ። ሲባም ንጉሡን፥ “እነሆ፥ የእስራኤል ቤት ዛሬ የአባቴን መንግሥት ይመልስልኛል ብሎ በኢየሩሳሌም ተቀምጦአል” አለው።
ንጉሡም ሲባን፥ “እነሆ፥ ለሜምፌቡስቴ የነበረው ሁሉ ለአንተ ይሁን” አለው። ሲባም ሰግዶ፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በፊትህ ሞገስን ላግኝ” አለ።
ከእርሱም ጋራ ከብንያም ወገን የሆኑ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ የሳኦልም ቤት አገልጋይ ሲባ ከእርሱም ጋር ዐሥራ አምስቱ ልጆቹና ሃያው አገልጋዮቹ ነበሩ፤ በንጉሡም ፊት በቀጥታ ወደ ዮርዳኖስ ሄዱ።
ንጉሡም፥ “የእግዚአብሔርን ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው አለን?” አለ። ሲባም ንጉሡን፥ “እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮናታን ልጅ አለ” አለው።
ወንድምም ሁሉ ያሰናክላልና፥ ባልንጀራም ሁሉ በጠማማነት ይሄዳልና እናንተ ሁሉ ከባልንጀሮቻችሁ ተጠንቀቁ፤ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ።
አንኩስም መልሶ ዳዊትን፥ “በዐይኔ ፊት ጻድቅ እንደ ሆንህ አውቃለሁ፤ ነገር ግን የፍልስጥኤማውያን አለቆች፦ ‘ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይወጣም’ አሉ።