ዘበኛውም ሌላ ሰው ሲሮጥ አየ፤ ዘበኛውም ለደጅ ጠባቂው ጮኾ፥ “እነሆ፥ ብቻውን የሚሮጥ ሌላ ሰው አየሁ” አለ። ንጉሡም፥ “እርሱ ደግሞ ወሬ ይዞ ይሆናል” አለ።
2 ሳሙኤል 18:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘበኛውም፥ “የፊተኛው ሩጫ እንደ ሳዶቅ ልጅ እንደ አኪማሖስ ሩጫ ይመስላል” አለ፤ “ንጉሡም፦ እርሱ መልካም ሰው ነው፤ መልካምም ወሬ ያመጣል” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠባቂውም፣ “የመጀመሪያው ሰው ሩጫ የሳዶቅን ልጅ የአኪማአስን ሩጫ ይመስለኛል” አለ። ንጉሡም፣ “እርሱማ ጥሩ ሰው ነው፤ የምሥራች ሳይዝ አይመጣም” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠባቂውም፥ “የመጀመሪያው ሰው ሩጫ የሳዶቅን ልጅ የአሒማዓጽን ሩጫ ይመስለኛል” አለ። ንጉሡም፥ “እርሱ ጥሩ ሰው ነው፤ ቢመጣም የምሥራች ይዞ ነው” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘበኛውም “የመጀመሪያው ሰው የሚሮጠው ልክ እንደ ሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽ ነው” አለ። ንጉሡም “እርሱ ጥሩ ሰው ነው፤ መልካም ወሬ ይዞ ይመጣል” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘበኛውም፦ የፊተኛው ሩጫ እንደ ሳዶቅ ልጅ እንደ አኪማአስ ሩጫ ይመስላል አለ፥ ንጉሡም እርሱ መልካም ሰው ነው፥ መልካም ወሬ ያመጣል አለ። |
ዘበኛውም ሌላ ሰው ሲሮጥ አየ፤ ዘበኛውም ለደጅ ጠባቂው ጮኾ፥ “እነሆ፥ ብቻውን የሚሮጥ ሌላ ሰው አየሁ” አለ። ንጉሡም፥ “እርሱ ደግሞ ወሬ ይዞ ይሆናል” አለ።
እርሱም ይህን ሲናገር የካህኑ የአብያታር ልጅ ዮናታን መጣ፤ አዶንያስም፥ “አንተ ኀያል ሰው ነህና፥ መልካምም ታወራልናለህና ግባ” አለው።
ሰላዩም፥ “መልእክተኛው ደረሰባቸው፥ ነገር ግን አልተመለሰም፤ የሚመራው ግን እንደ ናሜሲ ልጅ እንደ ኢዩ ይመራል በችኮላ ይሄዳልና” ብሎ ነገረው።
ሰላምን የሚያወራ፥ መልካም የምሥራችንም የሚናገር፥ መድኀኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም፥ “አምላክሽ ነግሦአል” የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።