2 ሳሙኤል 18:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም ለነገረው ሰው፥ “እነሆ፥ ካየኸው ለምን በምድር ላይ አልገደልኸውም? ዐሥር ብርና አንድ ድግ እሰጥህ ነበር” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአብም ይህን የነገረውን ሰው፣ “ምን አልህ! ካየኸው ታዲያ ለምንድን ነው ያኔውኑ መትተህ መሬት ላይ ያልጣልኸው? ይህን አድርገህ ቢሆን ኖሮ፣ ዐሥር ሰቅል ጥሬ ብርና የጀግና ሰው ቀበቶም እሸልምህ ነበር” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአብም ይህን የነገረውን ሰው፥ “ምን አልህ! ካየኸው ታዲያ ለምንድን ነው ያኔውኑ መተህ ምድር ላይ ያልጣልኸው? ይህን አድርገህ ቢሆን ኖሮ፥ ዐሥር ብርና ዝናር እሸልምህ ነበር” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብም “ታዲያ ካየኸው ለምን ወዲያውኑ አልገደልከውም? ይህን አድርገህ ቢሆን ኖሮ እኔ ራሴ ዐሥር ጥሬ ብርና አንድ ዙር ዝናር በሸለምኩህ ነበር” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም ለነገረው ሰው፦ እነሆ፥ ካየኸው ለምን ወደ ምድር አልመታኸውም? አሥር ብርና አንድ ድግ እሰጥህ ነበር አለው። |
ሰውየውም ኢዮአብን፥ “ንጉሡ አንተንና አቢሳን፥ ኤቲንም፦ ብላቴናውን አቤሴሎምን ጠብቁ ብሎ ሲያዝ እኛ በጆሮአችን ሰምተናልና ሺህ ሰቅል ብር በእጄ ላይ ብትመዝን እጄን በንጉሡ ልጅ ላይ አልዘረጋም ነበር።
ለአሚሳይም፦ አንተ የአጥንቴ ፍላጭና የሥጋዬ ቍራጭ አይደለህምን? በዘመንህም ሁሉ በኢዮአብ ፋንታ በፊቴ የሠራዊት አለቃ ሳትሆን ብትቀር ዛሬ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብኝ፤ ይህንም ይጨምርብኝ በሉት።”