2 ሳሙኤል 17:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሽራ ወደ ባልዋ እንደምትመለስ ሕዝቡን ሁሉ ወደ አንተ እመልሰዋለሁ፤ የአንድ ሰው ሰውነትን ብቻ ትሻለህና፤ ለሕዝቡ ሁሉ ግን ሰላም ይሆናል፤” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡን ሁሉ ወደ አንተ እመልሳለሁ፤ አንተ የምትፈልገው የአንድ ሰው ብቻ መሞት ሁሉም እንዲመለሱ ያደርጋል። ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ በሰላም ይኖራል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡን ሁሉ ወደ አንተ እመልሳለሁ፤ አንተ የምትፈልገው የአንድ ሰው መሞት ብቻ ነውና፥ ሕዝቡ ሁሉ በሰላም ይኖራል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሽራ ወደ ባልዋ እንደምትመለስ ተከታዮቹ በሙሉ ወደ አንተ ተመልሰው እንዲመጡ አደርጋለሁ፤ እንግዲህ አንተ የምትፈልገው አንድ ሰው ብቻ መግደልን ነው፤ የቀረው ሌላው ሕዝብ ግን በሰላም ይኖራል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሽራ ወደ ባልዋ እንደምትመለስ ሕዝቡን ሁሉ ወደ አንተ እመልሰዋለሁ፥ ሕዝቡ ሁሉ ደኅና ይሆናል፥ የምትፈልገው አንድ ሰው ብቻ ነው። |
አበኔርም ዳዊትን፥ “ተነሥቼ ልሂድ፤ ካንተ ጋርም ቃል ኪዳን እንዲያደርጉ፥ ነፍስህም እንደ ወደደች ሁሉን እንድትገዛ እስራኤልን ሁሉ ለጌታዬ ለንጉሥ ልሰብስብ” አለው። ዳዊትም አበኔርን አሰናበተው፤ በሰላምም ሄደ።