2 ሳሙኤል 17:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ወደ ምናሄም በመጣ ጊዜ በአሞን ልጆች ሀገር በአራቦት የነበረ የነዓሶን ልጅ ኡኤሴብ፥ የሎዶባርም ሰው የአሜሄል ልጅ ማኪር፥ የሮጌሌምም ሰው ገለዓዳዊው ቤርዜሊ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት መሃናይም ሲደርስ፣ ከአሞናውያን ከተማ ከረባት የመጣው፣ የናዖስ ልጅ ሾቢ፣ ከሎደባር የመጣው የዓሚኤል ልጅ ማኪርና ከሮግሊም የመጣው ገለዓዳዊው ቤርዜሊ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ማሕናይም ሲደርስ፥ ከአሞናውያን ከተማ ከራባ የመጣው፥ የናዖስ ልጅ ሾቢ፥ ከሎዶባር የመጣው የዓሚኤል ልጅ ማኪርና ከሮግሊም የመጣው ገለዓዳዊው ቤርዜሊ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት ማሕናይም በደረሰ ጊዜ በዐሞን ግዛት ራባ ተብላ ከምትጠራው ከተማ የመጣውን የናዖስን ልጅ ሾቢን፥ ከሎደባር ከተማ የመጣውን የዓሚኤልን ልጅ ማኪርንና ከገለዓድ ግዛት ሮገሊም ተብላ ከምትጠራው ከተማ የመጣውን ባርዚላይን አገኘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ወደ መሃናይም በመጣ ጊዜ በአሞን ልጆች አገር በረባት የነበረ የናዖስ ልጅ ኡኤስቢ፥ የሎዶባርም ሰው የዓሚኤል ልጅ ማኪር፥ የሮግሊምም ሰው ገለዓዳዊው ቤርዜሊ፦ |
ከወንድምህ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ ቀርበውኛልና ለገለዓዳዊው ለቤርዜሊ ልጆች ቸርነትን አድርግላቸው። በማዕድህም ከሚበሉት መካከል ይሁኑ።
ከካህናቱም ልጆች፤ የአብያ ልጆች፥ የአቆስ ልጆች፥ ከገለዓዳዊው ከቤርዜሊ ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስማቸውም የተጠራ የቤርዜሊ ልጆች።
እንዲህም ሆነ፤ ከአንድ ወር በኋላ አሞናዊው ናዖስ መጣ፤ በኢያቢስ ገለዓድም ሰፈረ፤ የኢያቢስም ሰዎች ሁሉ፥ “አሞናዊውን ናዖስን ቃል ኪዳን አድርግልን፤ እኛም እንገዛልሃለን” አሉት።