ከሄዱም በኋላ እነርሱ ከጕድጓዱ ወጥተው ሄዱ፤ ለንጉሡም ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትንም፥ “አኪጦፌል በእናንተ ላይ እንዲህ መክሮአልና ተነሡ፤ ፈጥናችሁም ውኃውን ተሻገሩ” አሉት።
2 ሳሙኤል 17:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አርካዊው ኩሲም ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር፥ “አኪጦፌል ለአቤሴሎምና ለእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህና እንዲህ መክሮአል፤ እኔ ግን እንዲህና እንዲያ መክሬአለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኩሲም ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን እንዲህ አላቸው፤ “አኪጦፌል አቤሴሎምንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ምን ምን ማድረግ እንዳለባቸው መክሯቸው ነበር፤ እኔ ግን እንዲህ እንዲህ አድርጉ ብዬ መክሬአቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሑሻይ ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን እንዲህ አላቸው፥ “አኪጦፌል አቤሴሎምንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች እንዲህ እንዲህ አድርጉ ሲል መክሮአቸው ነበር፤ እኔ ግን እንዲህ እንዲህ አድርጉ ብዬ መክሬአቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እርሱና አኪጦፌል ለአቤሴሎምና ለእስራኤላውያን መሪዎች የሰጡትን ምክር ሑሻይ ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር ነገራቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኩሲም ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር፦ አኪጦፌል ለአቤሴሎምና ለእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህና እንዲህ መክሮአል፥ እኔ ግን እንዲህና እንዲህ መክሬአለሁ። |
ከሄዱም በኋላ እነርሱ ከጕድጓዱ ወጥተው ሄዱ፤ ለንጉሡም ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትንም፥ “አኪጦፌል በእናንተ ላይ እንዲህ መክሮአልና ተነሡ፤ ፈጥናችሁም ውኃውን ተሻገሩ” አሉት።