ኢዮአብም በምድር ላይ በግንባሩ ወድቆ ሰገደለት፤ ንጉሡንም አመሰገነ፤ ኢዮአብም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የአገልጋይህን ነገር አድርገሃልና በዐይንህ ፊት ሞገስን እንዳገኘ አገልጋይህ ዛሬ ዐወቀ” አለ።
2 ሳሙኤል 16:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ሲባን፥ “እነሆ፥ ለሜምፌቡስቴ የነበረው ሁሉ ለአንተ ይሁን” አለው። ሲባም ሰግዶ፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በፊትህ ሞገስን ላግኝ” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ንጉሡ ሲባን፣ “የሜምፊቦስቴ የነበረው ሁሉ ከእንግዲህ ያንተ ነው” አለው። ሲባም፣ “በታላቅ ትሕትና በግንባሬ ተደፍቼ እጅ እነሣለሁ፤ ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ በፊትህ ሞገስ ላግኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ንጉሡ ጺባን፥ “የመፊቦሼት የነበረው ሁሉ ከእንግዲህ ያንተ ነው” አለው። ጺባም፥ “እጅ እነሣለሁ፤ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፤ በፊትህ ሞገስ ላግኝ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም ጺባን “የመፊቦሼት የነበረው ንብረት ሁሉ ከእንግዲህ የአንተ ነው” አለው። ጺባም “ንጉሥ ሆይ! እነሆ እኔ አገልጋይህ ነኝ፤ ዘወትር አንተን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ለመሥራት እተጋለሁ!” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ሲባን፦ እነሆ፥ ለሜምፊቦስቴ የነበረው ሁሉ ለአንተ ይሁን አለው። ሲባም፦ እጅ እነሣለሁ፥ ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በፊትህ ሞገስ ላግኝ አለ። |
ኢዮአብም በምድር ላይ በግንባሩ ወድቆ ሰገደለት፤ ንጉሡንም አመሰገነ፤ ኢዮአብም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የአገልጋይህን ነገር አድርገሃልና በዐይንህ ፊት ሞገስን እንዳገኘ አገልጋይህ ዛሬ ዐወቀ” አለ።
እንዲሁም የቴቁሔዪቱ ሴት ወደ ንጉሥ ገብታ በግንባርዋ በምድር ላይ ወደቀች፤ ሰግዳም “ንጉሥ ሆይ፥ አድነኝ፤ አድነኝ” አለች።
ንጉሡም፥ “የጌታህ ልጅ ወዴት ነው?” አለ። ሲባም ንጉሡን፥ “እነሆ፥ የእስራኤል ቤት ዛሬ የአባቴን መንግሥት ይመልስልኛል ብሎ በኢየሩሳሌም ተቀምጦአል” አለው።
ንጉሡ ዳዊትም ወደ በውሪም መጣ፤ እነሆም፥ ሳሚ የሚባል የጌራ ልጅ ከሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ከዚያ ወጣ፤ እየሄደም ይረግመው ነበር።
እርሱም በእኔ በባሪያህ ላይ ክፉ አደረገ፤ አንተ ጌታዬ ንጉሥ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነህ፤ በፊትህም ደስ ያሰኘህን አድርግ።
የሳኦልም ልጅ የዮናታን ልጅ ሜምፌቡስቴ ወደ ዳዊት መጣ፤ በግንባሩም ወድቆ ሰገደለት፤ ንጉሥ ዳዊትም፥ “ሜምፌቡስቴ ሆይ፥” አለ፤ እርሱም፥ “እነሆኝ አገልጋይህ” አለ።
“ስለ በደል ሁሉ፥ ክፉ በማድረግም ስለሚሠራት ኀጢአት ሁሉ በማንም ላይ አንድ ምስክር አይሁን፤ በሁለት ምስክሮች ወይም በሦስት ምስክሮች ቃል ነገር ሁሉ ይጸናል።