ዳዊትም ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም ያሉትን አገልጋዮቹን ሁሉ፥ “ተነሡ እንሽሽ፤ ከአቤሴሎም እጅ የምንድንበት የለንምና፤ ፈጥኖ እንዳይዘን፥ ክፉም እንዳያመጣብን፤ ከተማዪቱንም በሰልፍ ስለት እንዳይመታ ፈጥናችሁ እንሂድ” አላቸው።
2 ሳሙኤል 15:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የንጉሡም ብላቴኖች ንጉሡን፥ “እነሆ፥ ጌታችን ንጉሥ የመረጠውን ሁሉ እኛ አገልጋዮችህ እናደርጋለን” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንጉሡ ሹማምትም፣ “ጌታችን ንጉሡ የመረጠውን ሁሉ ለማድረግ እኛ አገልጋዮችህ ዝግጁ ነን” ብለው መለሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንጉሡ አገልጋዮቹም፥ “ጌታችን ንጉሡ የመረጠውን ሁሉ ለማድረግ እኛ አገልጋዮችህ ዝግጁ ነን” ብለው መለሱለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “እሺ ንጉሥ ሆይ! አንተ ያልከውን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁዎች ነን” ሲሉ መለሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የንጉሡም ባሪያዎች ንጉሡን፦ እነሆ፥ ጌታችን ንጉሡ የመረጠውን ሁሉ እኛ ባሪያዎችህ እሺ ብለን እናደርጋለን አሉት። |
ዳዊትም ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም ያሉትን አገልጋዮቹን ሁሉ፥ “ተነሡ እንሽሽ፤ ከአቤሴሎም እጅ የምንድንበት የለንምና፤ ፈጥኖ እንዳይዘን፥ ክፉም እንዳያመጣብን፤ ከተማዪቱንም በሰልፍ ስለት እንዳይመታ ፈጥናችሁ እንሂድ” አላቸው።
ሲባም ንጉሡን፥ “ጌታዬ ንጉሡ አገልጋዩን እንዳዘዘ እንዲሁ አገልጋይህ ያደርጋል” አለው። ሜምፌቡስቴም ከንጉሡ ልጆች እንደ አንዱ ከዳዊት ገበታ ይበላ ነበር።