ዘመንዋም በተፈጸመ ጊዜ የይሁዳ ሚስት ሴዋ ሞተች፤ ይሁዳም ተጽናና፤ የበጎቹን ጠጕር ወደሚሸልቱት ሰዎችም ወደ ተምና ወጣ፤ እርሱም ዓዶሎማዊው በግ ጠባቂው ኤራስም።
2 ሳሙኤል 13:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሴሎምም ወደ ንጉሡ መጥቶ፥ “እነሆ፥ አገልጋይህ በጎቹን ያሸልታል፤ ንጉሡ ከአገልጋይህ ጋር ይሂድ፤ አገልጋዮቹም ይሂዱ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቤሴሎምም ወደ ንጉሡ ሄዶ፣ “እነሆ፤ ባሪያህ በጎቹን እየሸለተ ነው፤ ታዲያ ንጉሡና ሹማምቱ ፈቃዳቸው ሆኖ እባክህ ይገኙልኝ?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ንጉሡም ሄዶ፥ “እነሆ፤ አገልጋይህ በጎቹን ይሸልታል፤ ንጉሡና ሹማምንቱ ፈቃዳቸው ሆኖ እባክህ ይገኙልኝ?” ሲል ጠየቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ንጉሥ ዳዊትም ሄዶ “ንጉሥ ሆይ! በጎቼን እየሸለትሁ ነው፤ ስለዚህ አንተና መኳንንትህ መጥታችሁ የግብዣው ተካፋዮች እንድትሆኑልኝ ትፈቅዳለህን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤሴሎምም ወደ ንጉሡ መጥቶ፦ እነሆ፥ ባሪያህ በጎቹን ያሸልታል፥ ንጉሡና ሎሌዎቹ ከባሪያህ ጋር ይሂዱ አለው። |
ዘመንዋም በተፈጸመ ጊዜ የይሁዳ ሚስት ሴዋ ሞተች፤ ይሁዳም ተጽናና፤ የበጎቹን ጠጕር ወደሚሸልቱት ሰዎችም ወደ ተምና ወጣ፤ እርሱም ዓዶሎማዊው በግ ጠባቂው ኤራስም።
ከሁለት ዓመትም በኋላ አቤሴሎም በኤፍሬም አቅራቢያ ባለችው በቤላሶር በጎቹን በሚያሸልትበት ጊዜ አቤሴሎም የንጉሡን ልጆች ሁሉ ጠራ።
ንጉሡም አቤሴሎምን፥ “ልጄ ሆይ፥ አይሆንም፤ እንከብድብሃለንና ሁላችን አንሄድም” አለው። የግድም አለው፤ እርሱ ግን መረቀው እንጂ ለመሄድ እንቢ አለ።
አሁንም በጎችህ እንደሚሸለቱ ከእኛ ጋር በምድረ በዳ ያሉ ሰዎች ነገሩን፤ እኛም አልከለከልናቸውም፤ በቀርሜሎስም በነበሩበት ዘመን ሁሉ ከመንጋቸው ይሰጡን ዘንድ አላዘዝናቸውም።