2 ሳሙኤል 13:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድምዋም አቤሴሎም፥ “ወንድምሽ አምኖን ከአንቺ ጋር ነበርን? እኅቴ ሆይ፥ አሁን ግን ዝም በዪ፤ ወንድምሽ ነውና፤ ይህን ነገር ትናገሪ ዘንድ በልብሽ አታስቢ” አላት። ትዕማርም በወንድምዋ በአቤሴሎም ቤት መበለት ሆና ተቀመጠች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሟ አቤሴሎምም፣ “ያ ወንድምሽ አምኖን ካንቺ ጋራ ነበርን? እኅቴ ሆይ፣ አሁን ዝም በዪ፤ ወንድምሽ ስለ ሆነ፤ ነገሩን በልብሽ አትያዢው” አላት። ትዕማርም በወንድሟ በአቤሴሎም ቤት ብቸኛ ሴት ሆና ኖረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሟ አቤሴሎምም፥ “ወንድምሽ አምኖን ከአንቺ ጋር ነበርን? እኅቴ ሆይ፥ በይ አሁን ዝም በዪ፤ ወንድምሽ ስለሆነ፥ ነገሩን በልብሽ አትያዠው” አላት። ትዕማርም በወንድሟ በአቤሴሎም ቤት ብቸኛ ሴት ሆና ኖረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድምዋ አቤሴሎም ባያት ጊዜ “እኅቴ ሆይ! ወንድምሽ አምኖን አስነወረሽን? እባክሽ እንደዚህ አትበሳጪ፤ እርሱ ወንድምሽ ስለ ሆነ ለማንም አትናገሪ” አላት። ስለዚህ ትዕማር በወንድሟ በአቤሴሎም ቤት ከሰው የተለየች ብቸኛ ሆና ተቀመጠች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድምዋም አቤሴሎም፦ ወንድምሽ አምኖን ከአንቺ ጋር ነበረን? እኅቴ ሆይ፥ አሁን ግን ዝም በዪ፥ ወንድምሽ ነው፥ ይህን ነገር በልብሽ አትያዢው አላት። ትዕማርም በወንድምዋ በአቤሴሎም ቤት ብቻዋን ተቀመጠች። |
ልያ በመስጴጦምያ በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነዚህ ናቸው፤ ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ አራት ነፍስ ናቸው።
ትዕማርም አመድ ወስዳ በራስዋ ላይ ነሰነሰች፤ በላይዋ የነበረውንም ብዙ ኅብር ያለውን ልብስዋን ቀደደችው፤ እጅዋንም በራስዋ ላይ ጭና እየጮኸች ሄደች።
ንጉሡም ዳዊት ይህን ነገር ሁሉ ሰማ፤ እጅግም ተቈጣ፥ ነገር ግን የበኵር ልጁ ነበረና ስለ ወደደው የልጁን የአምኖንን ነፍስ አላሳዘነም።
ወንድሞቻችን፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ቍጣን አሳልፏት፥ “እኔ እበቀላለሁ፤ እኔ ብድራትን እከፍላለሁ ይላል እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአልና።