2 ሳሙኤል 11:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ጠራው፤ በፊቱም በላና ጠጣ፤ አሰከረውም፤ ነገር ግን በመሸ ጊዜ ወጥቶ ከጌታው አገልጋዮች ጋር በምንጣፉ ላይ ተኛ፤ ወደ ቤቱም አልወረደም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ዳዊት ራሱ ባለበት ግብዣ አድርጎለት በላ፤ ጠጣ፤ አሰከረውም፤ ሲመሽም ኦርዮን በምንጣፉ ላይ ለመተኛት የጌታው አሽከሮች ወዳሉበት ወጥቶ ሄደ እንጂ ወደ ቤቱ አልወረደም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱም ዳዊት ራሱ ባለበት ግብዣ አድርጎለት በላ፤ ጠጣ፤ አሰከረውም፤ ሲመሽም ኦርዮ በምንጣፉ ላይ ለመተኛት የጌታው አገልጋዮች ወዳሉበት ወጥቶ ሄደ እንጂ ወደ ቤቱ አልወረደም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ኦርዮን ራት ጋበዘውና እስኪሰክር ድረስ የወይን ጠጅ እንዲጠጣ አደረገው፤ በዚያም ሌሊት ኦርዮ በቤተ መንግሥቱ ዘበኞች ቤት ብርድ ልብሱን በማንጠፍ ተኝቶ ዐደረ እንጂ ወደ ቤቱ አልሄደም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ጠራው፦ በፊቱም በላና ጠጣ፥ አሰከረውም፥ ነገር ግን በመሸ ጊዜ ወጥቶ ከጌታው ባሪያዎች ጋር በምንጣፉ ላይ ተኛ፥ ወደ ቤቱም አልወረደም። |
አቤሴሎምም፥ “አንተ እንቢ ካልህ ወንድሜ አምኖን ከእኛ ጋር እንዲሄድ እለምንሃለሁ” አለ። ንጉሡም፥ “ከአንተ ጋር ለምን ይሄዳል?” አለው።