Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 11:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ዳዊትም ኦርዮን ራት ጋበዘውና እስኪሰክር ድረስ የወይን ጠጅ እንዲጠጣ አደረገው፤ በዚያም ሌሊት ኦርዮ በቤተ መንግሥቱ ዘበኞች ቤት ብርድ ልብሱን በማንጠፍ ተኝቶ ዐደረ እንጂ ወደ ቤቱ አልሄደም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 በማግስቱም ዳዊት ራሱ ባለበት ግብዣ አድርጎለት በላ፤ ጠጣ፤ አሰከረውም፤ ሲመሽም ኦርዮን በምንጣፉ ላይ ለመተኛት የጌታው አሽከሮች ወዳሉበት ወጥቶ ሄደ እንጂ ወደ ቤቱ አልወረደም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በማግስቱም ዳዊት ራሱ ባለበት ግብዣ አድርጎለት በላ፤ ጠጣ፤ አሰከረውም፤ ሲመሽም ኦርዮ በምንጣፉ ላይ ለመተኛት የጌታው አገልጋዮች ወዳሉበት ወጥቶ ሄደ እንጂ ወደ ቤቱ አልወረደም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ዳዊ​ትም ጠራው፤ በፊ​ቱም በላና ጠጣ፤ አሰ​ከ​ረ​ውም፤ ነገር ግን በመሸ ጊዜ ወጥቶ ከጌ​ታው አገ​ል​ጋ​ዮች ጋር በም​ን​ጣፉ ላይ ተኛ፤ ወደ ቤቱም አል​ወ​ረ​ደም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ዳዊትም ጠራው፦ በፊቱም በላና ጠጣ፥ አሰከረውም፥ ነገር ግን በመሸ ጊዜ ወጥቶ ከጌታው ባሪያዎች ጋር በምንጣፉ ላይ ተኛ፥ ወደ ቤቱም አልወረደም።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 11:13
7 Referencias Cruzadas  

ኀፍረተ ሥጋው ሲገለጥ ለማየት ለሰው ቊጣህን እንደ ጠንካራ መጠጥ የምትሰጥና እስኪሰክርም ድረስ የምታጠጣው አንተ ሰው ወዮልህ!


ወይን ጠጅ ፌዘኛ፥ ጠንካራ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋሉ፤ በእነርሱ ሱስ የተጠመደ ጥበበኛ ሊሆን አይችልም።


አሮንንም “ከቶ ይህ ሕዝብ ምን አድርጎህ ነው ይህን የመሰለ አስከፊ ኃጢአት እንዲሠራ ያደረግኸው?” አለው።


ኦርዮ ግን ወደ ቤቱ ሳይሄድ ከንጉሡ ክብር ዘበኞች ጋር በቤተ መንግሥቱ የቅጽር በር አጠገብ ተኝቶ ዐደረ፤


አቤሴሎም ግን “መልካም ነው! አንተ መምጣት ካልፈቀድህ ወንድሜ አምኖን እንዲመጣ አትፈቅድለትምን?” ሲል ጠየቀ። ንጉሡም “እርሱስ ቢሆን ለምን ይመጣል?” ሲል ጠየቀው።


ሐዘንና ትካዜ የሚደርስበት ማን ነው? ዘወትር ክርክርና ጭቅጭቅ የሚያነሣሣ ማን ነው? ምክንያቱን ሳያውቅ ተፈንክቶ የሚገኝ ማን ነው? ዐይኑ የሚቀላበት ማን ነው?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios