La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 10:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊ​ትም ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ሰባት መቶ ሰረ​ገ​ለ​ኞ​ችን፥ አርባ ሺህም ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ገደለ፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም አለቃ ሶቤ​ቅን መታ፤ እር​ሱም በዚያ ሞተ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሶርያውያንም ለጦርነት ተሰልፈው ዳዊትን በግንባር ገጠሙት፤ ይሁን እንጂ ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ሰባት መቶ ሠረገለኞችንና አርባ ሺሕ እግረኛ ወታደሮች ገደለባቸው። እንዲሁም የሰራዊታቸውን አዛዥ ሶባክን አቍስሎት ስለ ነበር፣ እዚያው ሞተ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይሁን እንጂ ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ሰባት መቶ ሠረገለኞችንና አርባ ሺህ ፈረሰኞችን ገደለባቸው። እንዲሁም የሠራዊታቸውን አዛዥ ሾባክን አቁስሎት ስለ ነበር እዚያው ሞተ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እስራኤላውያን ሶርያውያንን መልሰው አሳደዱአቸው፤ ዳዊትና ሠራዊቱ ሰባት መቶ የሶርያውያንን ሠረገለኞችንና አርባ ሺህ ፈረሰኞችን ገደሉ፤ እንዲሁም የጠላት ሠራዊት አለቃ የነበረውን ሾባክን መተው አቊስለውት ስለ ነበር እዚያው በጦር ሜዳው ላይ ሞተ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሶርያውያንም ከእስራኤል ፊት ሸሹ፥ ዳዊትም ከሶርያውያን ሰባት መቶ ሰረገለኞች አርባ ሺህም ፈረሰኞች ገደለ፥ የሠራዊቱንም አለቃ ሶባክን መታ፥ እርሱም በዚያ ሞተ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 10:18
10 Referencias Cruzadas  

ለዳ​ዊ​ትም ነገ​ሩት፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ግሮ ወደ ኤላም መጣ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም በዳ​ዊት ፊት ተሰ​ል​ፈው ከእ​ርሱ ጋር ተዋጉ።


ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ ሺህ ሰረ​ገ​ላ​ዎ​ችን፥ ሰባት ሺህ ፈረ​ሰ​ኞ​ችን፥ ሃያ ሺህም እግ​ረ​ኞ​ችን ያዘ፤ ዳዊ​ትም የሰ​ረ​ገ​ለ​ኛ​ውን ፈረስ ሁሉ ቋንጃ ቈረጠ፤ ለራ​ሱም መቶ ሰረ​ገ​ላ​ዎ​ችን ብቻ አስ​ቀረ።


ዳዊ​ትም የሲ​ባን ሰዎች በገ​ደለ ጊዜ ሬዞን ሰዎ​ችን ሰብ​ስቦ የጭ​ፍራ አለቃ ሆነ፤ ወደ ደማ​ስ​ቆም ሄዱ፥ በዚ​ያም ተቀ​መጡ፤ በደ​ማ​ስ​ቆም ላይ አነ​ገ​ሡት።


ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ከዳ​ዊት ፊት ሸሹ፤ ዳዊ​ትም ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ሰባት ሺህ ሰረ​ገ​ለ​ኞ​ችን፥ አርባ ሺህም እግ​ረ​ኞ​ችን ገደለ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም አለቃ ሶፋ​ክን ገደለ።


በጥ​ልቅ ረግ​ረግ ጠለ​ቅሁ ኀይ​ልም የለ​ኝም፤ ወደ ጥልቁ ባሕ​ርም ደረ​ስሁ ማዕ​በ​ሉም አሰ​ጠ​መኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሦር በነ​ገ​ሠው በከ​ነ​ዓን ንጉሥ በኢ​ያ​ቢን እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ሲሣራ ነበረ፤ እር​ሱም በአ​ሕ​ዛብ አሪ​ሶት ይቀ​መጥ ነበረ።


እነ​ሆም፥ ባርቅ ሲሣ​ራን ሲያ​ባ​ርር ኢያ​ዔል ልት​ገ​ና​ኘው ወጥታ፥ “ና፤ የም​ት​ሻ​ውን ሰው አሳ​ይ​ሃ​ለሁ” አለ​ችው። ወደ እር​ስ​ዋም ገባ፤ እነ​ሆም፥ ሲሣ​ራን ወድቆ፥ ሞቶም አገ​ኘው፤ ካስ​ማ​ውም በጆሮ ግንዱ ውስጥ ነበረ።


ግራ እጅ​ዋን ወደ ካስማ፤ ቀኝ እጅ​ዋ​ንም ወደ ሠራ​ተኛ መዶሻ አደ​ረ​ገች፤ በመ​ዶ​ሻ​ውም ሲሣ​ራን መታ​ችው፤ ራሱ​ንም ቸነ​ከ​ረች፤ ጆሮ ግን​ዱ​ንም በሳች፤ ጐዳ​ች​ውም።