Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 5:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ግራ እጅ​ዋን ወደ ካስማ፤ ቀኝ እጅ​ዋ​ንም ወደ ሠራ​ተኛ መዶሻ አደ​ረ​ገች፤ በመ​ዶ​ሻ​ውም ሲሣ​ራን መታ​ችው፤ ራሱ​ንም ቸነ​ከ​ረች፤ ጆሮ ግን​ዱ​ንም በሳች፤ ጐዳ​ች​ውም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 እጇ ካስማ ያዘ፤ ቀኝ እጇም የሠራተኛ መዶሻ ጨበጠ፤ ሲሣራን መታችው፤ ራሱንም ተረከከችው፤ ክፉኛ ወጋችው፤ ጆሮ ግንዱን በሳችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 እጅዋን ወደ ካስማ፥ ቀኝ እጅዋንም ወደ ሠራተኛ መዶሻ አደረገች፥ በመዶሻውም ሲሣራን መታች፥ ራሱንም ቸነከረች፥ ጆሮግንዱንም በሳች፥ ጎዳችውም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እንዲሁም በአንድ እጅዋ የድንኳን ካስማ፥ በቀኝ እጅዋ የሠራተኛ መዶሻ ያዘች፤ ሲሣራንም መታ የራስ ቅሉን አደቀቀችው፤ ጆሮ ግንዱንም ቸነከረችው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እጅዋን ወደ ካስማ፥ ቀኝ እጅዋንም ወደ ሠራተኛ መዶሻ አደረገች፥ በመዶሻውም ሲሣራን መታች፥ ራሱንም ቸነከረች፥ ጆሮግንዱንም በሳች፥ ጎዳችውም።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 5:26
5 Referencias Cruzadas  

ያቺም ሴት ወደ ሕዝቡ ሁሉ ገብታ ለከ​ተ​ማው ሕዝብ ሁሉ በብ​ል​ሀት ነገ​ረ​ቻ​ቸው፤ የቢ​ኮ​ሪን ልጅ የሳ​ቡ​ሄን ራስ ቈር​ጠው ሰጡ​አት፤ ወደ ኢዮ​አ​ብም ጣለ​ችው። ኢዮ​አ​ብም መለ​ከ​ቱን ነፋ፤ ሰውም ሁሉ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ርቆ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ድን​ኳኑ ሄደ። ኢዮ​አ​ብም ወደ ንጉሡ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሰ።


የሔ​ቤ​ርም ሚስት ኢያ​ዔል የድ​ን​ኳ​ኑን ካስማ ወሰ​ደች፤ በሁ​ለ​ተኛ እጅ​ዋም መዶሻ ያዘች፤ ቀስ ብላም ወደ እርሱ ቀረ​በች፤ በጆሮ ግን​ዱም ካስ​ማ​ውን ቸነ​ከ​ረ​ች​በት፤ እር​ሱም ደክሞ አን​ቀ​ላ​ፍቶ ነበ​ርና ካስ​ማው ወደ መሬት ጠለቀ፤ እር​ሱም ከእ​ግ​ርዋ በታች ተን​ፈ​ራ​ፈረ፤ ተዘ​ር​ሮም ሞተ።


ውኃ ለመነ፤ ወተ​ትም ሰጠ​ችው፤ በተ​ከ​በረ ዳካ እርጎ አቀ​ረ​በ​ች​ለት።


በእ​ግ​ሮ​ችዋ አጠ​ገብ ተደፋ፤ ወደቀ፤ ተኛ፤ በእ​ግ​ሮ​ችዋ አጠ​ገብ ተፈ​ራ​ገጠ፤ በተ​ፈ​ራ​ገ​ጠ​በ​ትም በዚያ ተጐ​ሳ​ቍሎ ሞተ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos