እንዲሁም የቴቁሔዪቱ ሴት ወደ ንጉሥ ገብታ በግንባርዋ በምድር ላይ ወደቀች፤ ሰግዳም “ንጉሥ ሆይ፥ አድነኝ፤ አድነኝ” አለች።
2 ነገሥት 8:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባቱም ዓመት ካለፈ በኋላ ያች ሴት ከፍልስጥኤም ሀገር ተመለሰች፤ ሄዳም ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ልትጮህ ወደ ንጉሡ ወጣች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰባት ዓመት በኋላም፣ ከፍልስጥኤም ምድር ተመልሳ መጣች፤ ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ አቤቱታ ለማቅረብም ወደ ንጉሡ ሄደች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰባቱም የራብ ዓመቶች ፍጻሜ በኋላ ወደ እስራኤል ተመለሰች፤ መኖሪያ ቤትዋና የእርሻ መሬትዋ እንዲመለስላት ለመጠየቅ ወደ ንጉሡ ቀረበች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰባቱም የራብ ዓመቶች ፍጻሜ በኋላ ወደ እስራኤል ተመለሰች፤ መኖሪያ ቤትዋና የእርሻ መሬትዋ እንዲመለስላት ለመጠየቅ ወደ ንጉሡ ቀረበች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባቱም ዓመት በተፈጸመ ጊዜ ሴቲቱ ከፍልስጥኤም አገር ተመለሰች፤ ስለ ቤትዋና ስለ መሬትዋ ልትጮኽ ወደ ንጉሡ ወጣች። |
እንዲሁም የቴቁሔዪቱ ሴት ወደ ንጉሥ ገብታ በግንባርዋ በምድር ላይ ወደቀች፤ ሰግዳም “ንጉሥ ሆይ፥ አድነኝ፤ አድነኝ” አለች።
እርሱም፥ “እነሆ፥ ይህን ሁሉ ክብር አከበርሽኝ ምን ላድርግልሽ? ለንጉሥ ወይስ ለሠራዊት አለቃ የምነግርልሽ ጉዳይ እንዳለሽ በላት” አለው፤ እርስዋም፥ “እኔ በወገኔ መካከል እኖራለሁ” ብላ መለሰች።
ንጉሡም የእግዚአብሔር ሰው የኤልሳዕ ሎሌ ግያዝን፥ “ኤልሳዕ ያደረገውን ታላላቅ ተአምራት ሁሉ ንገረኝ” እያለ ይነጋገር ነበር።
ንጉሡም ሴቲቱን ጠየቃት፤ እርስዋም ነገረችው። ንጉሡም ከባለሟሎቹ አንዱን ሰጣት፤ “እህልዋንና ገንዘብዋን ሁሉ ሀገሩን ከተወች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የሄደ ቦታዋን ሁሉ መልስላት” አለው።
የድሃውንና የችግረኛውን ፍርድ ይፈርድ ነበር፤ በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖ ነበር። ይህ እኔን ማወቅ አይደለምን? ይላል እግዚአብሔር።