ግያዝንም ጠርቶ፥ “ይህችን ሱማናዊት ጥራ” አለው። ጠራትም፤ ወደ እርሱም በገባች ጊዜ፥ “ልጅሽን አንሥተሽ ውሰጂ” አላት።
2 ነገሥት 6:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “እነሆ፥ ምሳርህ ውሰደው” አለ፤ እጁንም ዘርግቶ ወሰደው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም፣ “በል አውጣና ውሰደው” አለው፤ ሰውየውም እጁን ዘርግቶ ወሰደው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ “አውጥተህ ውሰድ” አለው፤ ሰውየውም ጐንበስ ብሎ አነሣው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ “አውጥተህ ውሰድ” አለው፤ ሰውየውም ጐንበስ ብሎ አነሣው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም “ውሰደው፤ አለ፤ እጁንም ዘርግቶ ወሰደው። |
ግያዝንም ጠርቶ፥ “ይህችን ሱማናዊት ጥራ” አለው። ጠራትም፤ ወደ እርሱም በገባች ጊዜ፥ “ልጅሽን አንሥተሽ ውሰጂ” አላት።
መጥታም ለእግዚአብሔር ሰው ነገረችው፤ እርሱም፥ “ሄደሽ ዘይቱን ሽጭ ዕዳሽንም ክፈዪ፤ በተረፈውም ዘይት የአንቺንና የልጆችሽን ሰውነት አድኚ” አላት።
የእግዚአብሔርም ሰው፥ “የወደቀው ወዴት ነው?” አለ፤ ስፍራውንም አሳየው፤ ከእንጨትም ቅርፊት ቀርፎ በዚያ ጣለው፤ ብረቱም ተንሳፈፈ።
የሶርያም ንጉሥ ከእስራኤል ጋር ይዋጋ ነበር፤ ከአገልጋዮቹም ጋር ተማክሮ፥ “በዚህ ስውር ቦታ ተደብቀን እናድራለን።” አላቸው።
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “እጅህን ዘርግተህ ጅራቱን ያዝ” አለው፤ ሙሴም እጁን ዘርግቶ፥ ጅራቱን ይዞ፥ አነሣው በእጁም በትር ሆነ።