2 ነገሥት 4:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ሰዎቹ ይበሉ ዘንድ አቀረበላቸው፤ የበሰለውንም ቅጠል በሚበሉበት ጊዜ፥ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ በምንቸቱ ውስጥ መርዝ አለ” ብለው ጮኹ፤ ይበሉም ዘንድ አልቻሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹ እንዲመገቡትም ወጡ ወጣ፤ ገና አንደ ቀመሱትም፣ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፤ በምንቸቱ ውስጥ የሚገድል መርዝ አለ!” ብለው ጮኹ፤ ሊመገቡትም አልቻሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነቢያትም እንዲመገቡት የወጣላቸውን ወጥ ቀምሰው “በዚህ ወጥ ውስጥ የሚገድል መርዝ አለ!” ብለው ወደ ኤልሳዕ ጮኹ፤ ሊመገቡትም አልቻሉም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነቢያትም እንዲመገቡት የወጣላቸውን ወጥ ቀምሰው “በዚህ ወጥ ውስጥ የሚገድል መርዝ አለ!” ብለው ወደ ኤልሳዕ ጮኹ፤ ሊመገቡትም አልቻሉም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎቹም ይበሉ ዘንድ ቀዱ፤ ወጡንም በቀመሱ ጊዜ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! በምንቸቱ ውስጥ ሞት አለ፤” ብለው ጮኹ፤ ይበሉም ዘንድ አልቻሉም። |
እርስዋም ኤልያስን፥ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? አንተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ፥ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን?” አለችው።
ደግሞም ሌላ የአምሳ አለቃ ከአምሳ ሰዎች ጋር ላከበት፤ የአምሳ አለቃውም፥ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ንጉሡ፦ ና፤ ፈጥነህ ውረድ ይላል” ብሎ ተናገረ።
ንጉሡም ደግሞ ሦስተኛ የአምሳ አለቃ ከአምሳ ሰዎች ጋር ላከ፤ ሦስተኛውም የአምሳ አለቃ ወጥቶ በኤልያስ ፊት በጕልበቱ ተንበረከከና ለመነው እንዲህም አለው፥ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ሰውነቴና የእነዚህ የአምሳው ባሪያዎችህ ሰውነት በፊትህ የከበረች ትሁን።
ንጉሡም ይጠሩት ዘንድ የአምሳ አለቃውን ከአምሳ ሰዎች ጋር ወደ እርሱ ላከ፤ ወደ እርሱም ሄዱ፤ እነሆም፥ በተራራ ራስ ላይ ተቀምጦ አገኙት። የአምሳ አለቃውም፥ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ንጉሡ ይጠራሃል ፈጥነህ ና፤ ውረድ” አለው።
አንዱም ቅጠላ ቅጠል ያመጣ ዘንድ ወደ ሜዳ ወጣ፤ በምድረ በዳውም የወይን ቦታ አገኘ፤ ከዚያም የምድር ቅጠላ ቅጠል ሰብሰበ፤ ልብሱንም ሞላ፤ መትሮም በወጡ ምንቸት ውስጥ ጨመረው፤ አበሰለውም፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላወቁም።
አሁን እንግዲህ እንደገና በዚህ ጊዜ ብቻ ኀጢአቴን ይቅር በሉኝ፤ ይህንም ሞት ብቻ ከእኔ ያነሣልኝ ዘንድ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ” አላቸው።